ኢለን መስክን እና ኬትሊን ጀነርን ጨምሮ ሌሎችም ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ደግሞ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ናቸው
ዝነኛ አሜሪካዊያን እና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ 47ኛውን ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ነገ ድምጽ በይፋ መስጠት ይጀመራል፡፡
ምርጫው ከዕጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ባለፈ በአሜሪካ እና በቀሪው ዓለም ዝነኛ የሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አስተያየት ለምርጫው ድምቀት ሆኗል፡፡
ከዲሞክራቷ ካማላ ጀርባ ዝነኛ ሙዚቀኞች ያሉ ሲሆን ለአብነትም የዓማችን ቁጥር አንድ የኪነ ጥበብ ባለጸጋዋ ቴይለር ስዊፍት፣ ቢዮንሴ፣ ጀኒፈር ሎፔዝ፣ የታይታኒኩ ሊኦናርዶ ዲካፕሪዮ እና ሌሎችም አሉ፡፡
እንዲሁም ከሪፐብሊካኑ ዶናድ ትራምፕ ጀርባ ደግሞ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋው ኢለን መስክ፣ ታዋቂው የፍልሚያ ስፖርተኛው ሀልክ ሆጋን፣ አምበር ሮዝ፣ኬትሊን ጀነር እና ሌሎችም አሉበት፡፡
እነዚህ ዝነኛ አሜሪካዊያን ከራሳቸው ባለፈ አድናቂዎቻቸው ለሚደግፏቸው እጩዎች ድምጻቸውን እንዲሰጡ ተጽዕኖ እያሳደሩ ይገኛሉ፡፡