ምርጫ2012 በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መራዘሙን ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
ምርጫ2012 በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መራዘሙን ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
የዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንደማይካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
ምርጫው ነሀሴ 23፣2012ዓ.ም እንዲካሄድ እቅድ ተይዞለት ነበር፡፡ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ከስቀመጠ በኋላ ለምርጫ የሚሆኑ ግብአቶችን በማሟላት ሂደት ላይ እንደነበረ ሲገልጽ ነበር፡፡
ነገርግን ቦርዱ አለምአቀፋዊ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ምክንያት የተያዘውን የጊዜ ሰሌዳ በመሰረዝ በሰሌዳው መሰረት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ለጊዜው እንዲቆሙ መወሰኑን አስታውቋል።