አምባሳደር ሽፈራው ይህንን ክስተት አስመልክቶ ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሞዛምቢክ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር በቅርብ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል
አምባሳደር ሽፈራው ይህንን ክስተት አስመልክቶ ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሞዛምቢክ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር በቅርብ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል
ከማላዊ ወደ ሞዘምቢክ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ውስጥ ከተፈጠረ የመተፋፈን አደጋ በህይወት የተረፉ 14 ኢትዮጵያውያን በሰሜን ሞዛምቢክ እንደሚገኙ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
አምባሳደር ሽፈራው በኮንቴነር ሲጓዙ የነበሩት ዜጎቹ በመተፋፈግ መሞታቸውን ለአል-አይን አማርኛ አረጋግጠዋል፡፡
ከማላዊ ወደ ሞዘምቢክ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ውስጥ 64 ኢትዮጵያዊያን በመተፋፈን ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ የተገለጸ ሲሆን ሞተው የተገኙት በኮንቴነር ውስጥ ተጭነው ወደ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ ላይ ሳሉ መሆኑን አምባሳደሩ አብራርተዋል፡፡
አምባሳደሩ ይህንን ክስተት አስመልክቶ ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሞዛምቢክ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር በቅርብ እየሰራ መሆኑን ገልጸው የሟቾቹን ብዛት እና መሰል ዝርዝር መረጃዎች በቀጣይ ይገጻል ብለዋል፡፡
አምባሳደሩ ኢትዮጵያውያኑ ሲጓዙበት የነበረው መኪና አሽከርካሪ የጫነው ምን እንደሆነ ተጠይቆ ሸቀጣ ሸቀጥ እንደጫነ መግለጹን ያስታወቁ ሲሆን መዳረሻቸውም ደቡብ አፍሪካ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ በህይወት ያሉት በሞዛምቢክ ቴቴ በተባለችው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ህክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡