በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዛሬ እንደሚጀምር የኦሮሚያ ክልል አስታውቋል
በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዛሬ እንደሚጀምር የኦሮሚያ ክልል አስታውቋል
በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ዳግም እንዲጀምር መደረጉን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታውቋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፣ በአካባቢዎቹ የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም ወደ ስራ እንዲመለስ የክልሉ መንግስት እና የፌደራል መንግስት በጋራ ሲሰሩት የነበረው ስራ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
ይህንን ተከትሎም ከዛሬ ጀምሮ በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም አገልፍሎት እንዲጀምር ተወስኗል ብለዋል።
ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምእራብ ኦሮሚያ የተከሰተው የስልክና የኢንተርኔት መቋረጥ እንደሚያሳስበው ገልጾ ነበር፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ሩፔርት ኮለቪል የግንኙነት መቋረጥ (ኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት) ሰዎች ስለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅታዊ መረጃ እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል ማለታቸው ይታወሳል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠው በፀጥታ ችግር ምክንያት ነበር፡፡