ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች ሙሉ እውቅና ለመስጠት ሲጠይቅ የነበረውን ክፍያ ወደ 30ሺ ብር ከፍ አደረገ
ቦርዱ ለሙሉ እውቅና ለመስጠት ሲጠይቅ የነበረውን ክፍያ ከ200 ወደ 30ሺ ከፍ ማድረጉን አስታውቋል
ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሰጣቸው ሶስት አገልግሎቸቶች ላይ ከጥቅምት 11 ጅምሮ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል
ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች ሙሉ እውቅና ለመስጠት ሲጠይቅ የነበረውን ክፍያ ወደ 30ሺ ብር ከፍ አደረገ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሰጣቸው ሶስት አገልግሎቶች ላይ ከጥቅምት 11፣2017ዓ.ም ጅምሮ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።
ቦርዱ ጭማሪ ያደረገባቸው ሶስት አገልግሎቶች የጊዜያዊ እውቅና፣ የሙሉ እውቅና እና የሰነድ ማሻሻያ ክፍያዎች ናቸው።
የምርጫ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር አዋጅ ከወጣበት ከ2011 ጀምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለጊዜያዊ ሰርተፍኬት 100 ብር፣ ለሙሉ እውቅና 200 ብር እና የተመዘገቡ ፓርቲዎች ሰነዳቸውን ለማሻሻል 30 ብር ሲያስከፍል መቆየቱን ያስታወሰው ቦርዱ አሁን የክፍያ መጠኑን መጨመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ብሏል።
በአዲሱ "የክፍያ ማሻሻያ ተመን መሰረት" ለጊዜያዊ እውቅና 15ሺ ብር፣ ለሙሉ እውቅና 30ሺ ብር፣ ለሰነድ ማሻሻያ ደግሞ 5ሺ ብር እንደሚያስከፍል ቦርዱ ገልጿል።
የባለፈው ምርጫ 2013 ከመካሄዱ በፊት ሙሉ እውቅና ያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር 53 እንደነበር ቦርዱ በወቅቱ መረጃ አውጥቶ ነበር። ሙሉ እውቅና ካገኙት ውስጥ በምርጫው ለመወዳደር ምልክት ወስደው የነበሩት 49 ሲሆኑ ሁለቱ ዘግየት ብለው ከምርጫው ራሳቸውን አግለዋል።
ምርጫ ለፖለቲካ ፖርቲዎች የድጎማ በጀት የማከፋፈል ኃላፊነትም አለበት።