ኢሎን መስክ ከትዊተር ኩባንያ ከ30 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ማሰናበት መጀመራቸው ተነገረ
ትዊተር የስራ ኃይሉን ከተለያዩ ክፍሎች በሰፊው መቀነሱን ሰራተኞች ተናግረዋል
ትዊተር ለሰማያዊ ባጅ ወይም “ቬሪፊኬሽን” በወር ሊያስከፍል መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል
ትዊተርን በቅርቡ ጠቅልለው የግላቸው ያደረጉት የዓለማችን ቁጥር አንድ ቱጃር ኢሎን መስክ ከትዊተር ኩባንያ ከ30 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ማሰናበት መጀመራቸው ተነገረ።
ቲዊተር የስራ ኃይሉን ከተለያዩ ክፍሎች በሰፊው መቀነሱን ሰራተኞች ተናግረዋል ።
በ44 ቢሊየን ዶላር ግዙፉን የትስስር ገፅ የገዙት መስክ ለመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች የትዊተርን ሰራተኞች እስከ 75 በመቶ ለመቀነስ ስለመወጠናቸው ጠቁመዋል ነው የተባለው።
ኢሎን መስክ በትዊተር ላይ የጅምላ ማሰናበት እየጀመረ ሲሆን የኩባንያውን የ 7 ሽህ 500 የሰው ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ እና የኩባንያውን የጅምላ ማሻሻያ ሥራ መጀመራቸው ተነግሯል።
ባለፈው ሐሙስ ለኩባንያው ሰራተኞች በተላከ ኢሜል ከስራ የማሰናበት እቅድ እንዳላቸው አሳውቀዋል። አዲሱ የትዊተር ባለቤት፤ ሰራተኞች “በትዊተር ላይ ያለዎት ሚና” የሚል ርዕስ ያለው ኢሜል እንደሚደርሳቸው ተናግረዋል።
ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው ከሆነ በስራቸውን የሚቆዩ ሰዎች በኩባንያቸው ኢሜል ይነገራቸዋል። ከስራቸው የሚሰናበቱት ደግሞ በግል ኢሜይላቸው ዜናው እንደሚደርሳቸው ታውቋል።
ዋሽንግተን ፖስት አገኘኋቸው ባላቸው በርካታ የኢሜል ኩባንያው “ትዊተርን ጤናማ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰው ኃይሉን ለመቀነስ በአስቸጋሪው ሂደት ውስጥ ያልፋል” የሚል መልዕክት ተንፀባርቋል።
ኩባንያው ይህ ውሳኔ ጠቃሚ አስተዋፅዖ ያደረጉ በርካታ ሰራተኞች ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር እንገነዘባለን ያለም ሲሆን፤ ነገር ግን እርምጃ የኩባንያውን ስኬትና ወደፊት መጓዙን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ብሏል።
ኢሎን መስክ ከሳምንት በፊት በትዊተር ስራውን የጀመሩት የቀድሞ የኩባንያውን ስራ አስፈፃሚዎችን በማባረር ሲሆን ከእነዚህም መካከል ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ ዋና የፋይናንስ ኃላፊው እና አማካሪው ይገኙበታል።
የዓለማችን የኤሌክትሮኒክስ ተሸከርካሪዎችን አምራች የሆነው ቴስላ ኩባንያ እና ስታርሊንክ የተሰኘው የኮሙንኬሽን ሳተላይት ባለቤት ኤለን መስክ ትዊተርን በ44 ቢሊየን ዶላር ገዝተዋል።
ቁልፍ የኩባንያው አመራሮችን በማሰናበት ስራ የጀመሩ ኤለን መስክ የሰማያዊ ባጅ ወይም ቬሪፊኬሽን ለሚፈልጉ የትዊተር ተጠቃሚዎች አዲስ የክፍያ መንገድ እንዲዘረጋ ለሰራተኞቻቸው ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወሳል።
እንደ ኒዮርክ ፖስት ዘገባ ከሆነ ተዊተር ለቬሪፊኬሸን በወር 20 ዶላር ለማስከፈል እቅድ ያወጡ ሲሆን አገልግሎቱም ከፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር ከህዳር ሰባት ጀምሮ እንደሚተገበር ተገልጿል።