ኢሉን መስክ ይህን ያህል ገንዘብ ቢከስሩም አሁንም የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ናቸው
ኢሉን መስክ በአንድ ቀን 16 ቢሊዮን ዶላር ከሰሩ።
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆኑት አሜሪካዊው ኢሉን መስክ በአንድ ቀን 16 ቢሊዮን ዶላር መክሰራቸው ተገልጿል።
ባለጸጋው ኪሳራው የደረሰባቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን በማምረት የሚታወቀው ቴስላ ኩባንያ የአክስዮን ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
የ2023 የአለም 10 የሀብት ባለጸጋዎች (ቢሊየነሮች)
የቴስላ ኩባንያ አንድ አክስዮን ዋጋ ወደ 220 ዶላር ዝቅ ብሏል የተባለ ሲሆን አጠቃላይ የአክስዮን ዋጋው ደግሞ በ9 ነጥብ 3 በመቶ ቀንሷል ተብሏል።
የድርጅቱ አክስዮን ዋጋ ዝቅ ያለው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ያስመዘገበው ትርፍ ቀንሷል የሚል ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።
የአውሮፓ ህብረት በሩሲያውያን ባለጸጋዎች ላይ የጣለውን ማዕቀብ አነሳ
በአንድ ቀን 16 ቢሊዮን ዶላር የከሰረው ኢሉን መስክ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ ወደ 192 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ቢልም አሁንም ቁጥር አንድ የዓለማችን ባለጸጋነት ደረጃን እንደያዘ ነው ተብሏል።
ፈረንሳዊው የፋሺን ኢንዱስትሪ ሰው በርናርድ አርኖልት በ191 ቢሊዮን ዶላር ሁለተኛው የዓለማችን ባለጸጋ ናቸው።
ኢሉን መስክ በበርናርድ አርኖልት ደረጃቸውን ተነጥቀው የነበሩ ቢሆንም መልሰው ደረጃውን መቆጣጠር ችለዋል።
የዓለም ባለጸግነት ደረጃን እስከ አስረኛ ድረስ ካሉት ሀብታም ሰዎች መካከል ስድስቱ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦች ናቸው።