ፖለቲካ
አሜሪካ የኢለን መስክ 'ስፔስ ኤክስ' ኩባንያ በሰራተኛ ቅጥር አድልዎ ከሰሰች
ስፔስ ኤክስ ፍልሰተኞችና ጥገኝነት ያገኙ ሰዎች ስራ እንዳይቀጠሩ ከልክሏል ተብሏል
ኩባንያው ከጠፈር ምህንድስና እስከ ምግብ አብሳይነት ያሉ ስራዎችን ነው የከለከለው
የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ 'ስፔስ ኤክስ' የተባለው የኢለን መስክ ኩባንያ ሰራተኛ ሲቀጥር ፍልሰተኞችና ጥገኝነት ያገኙት ላይ አድልዎ ፈጽሟል በሚል ክስ መመስረቱን አስታውቋል።
ኩባንያው የአሜሪካ ዜግነት የሌላቸውን ሰዎች መቅጠር እንደማይችል በሀሰት ሲያሰራጭ ነበር ብሏል።
ፍትህ ቢሮው ሰራተኞች አድልዎ እንደደረሰባቸው ካመለከቱ በኋላ ኩባንያው ላይ ምርመራ መጀመሩን ተናግሯል።
ከመስከረም 2018 እስከ ግንቦት 2022 ድረስ ስፔስ ኤክስ ፍልሰተኞችና ጥገኝነት ያገኙ ሰዎች ስራ እንዳያመለክቱና እንዳይቀጠሩ ከልክሏል ነው የተባለው።
ኩባንያው አግልሏቸዋል የተባሉ ሰዎች በሀገሪቱ የመስራት መብት ያላቸው ናቸው ተብሏል።
ቢሮው ስፔስ ኤክስ በ"ወጪ ንግድ ህግ" ዜጋ የሆኑትንና ግሪን ካርድ ያላቸውን ሰዎች ብቻ መቅጠር እንደሚፈቀድለት የኢለን መስኩ ኩባንያ ተናግሯል።
እንደዚህ የሚል ህግ እንደሌለም ፍትህ ቢሮ ገልጿል።
ፍልሰተኞችና ጥገኝነት ያገኙ ሰዎች ከጠፈር ምህንድስና እስከ ምግብ አብሳይነት ያሉ ስራዎችን ነው መቀጠር ያልቻሉት።