መስክ ባለፈው ህዳር ወር አጋማሽ ጀዊሾች በነጮች ላይ ጥላቻ እንዳላቸው በሚገልጽ የኤክስ ፖስት ላይ ስምምነቱን በግለጹ ምክንያት ከፍተኛ ትችት አስተናግዷል
ኢሎን መስክ የጋዛ ታጋቾችን ምልክት ለመልበስ ቃል ገባ
በኤክስ ላይ በተፖሰተ ጸረ-ሴማዊ ይዘት ባለው ጹሁፍ ምክንያት ከፍተኛ ትችት ካስተናገደ በኋላ እስራኤልን እየጎበኘ የሚገኘው መስክ በጋዛ ልጃቸው ከታገተባቸው አባት ምልክት (የብረት ታግ) መቀበሉን ሮይተርስ ዘግቧል።
መስክ ሁሉም ታጋቾች እስከሚለቀቁ ድረስ የታጋቾቹን ምልክት እንደሚለብሰው ቃል ገብቷል።
ኦመር ሸም ቶቭ የተባለ ልጃቸው ከታገተባቸው ማልኪ ሸም ቶቭ የተቀበለው ምልክት "ልባችን በጋዛ ታግቷል" የሚል ጹሁፍ እንዳለበት መስክ የእስራኤልን ፕሬዝደንት ኢሳሀቅ ሄርዞግን ቢሮ ሲጎበኝ በሚያሳየው ቨዲዮ ታይቷል።
ምልክቱ ባለፈው ጥቅምት ወር ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ 240 ሰዎችን አግቶ ወደ ጋዛ ከወሰደ በኋላ በመላው እስራኤል በብዛት የሚታይ ነው።
መስክ ባለፈው ህዳር ወር አጋማሽ ጀዊሾች በነጮች ላይ ጥላቻ እንዳላቸው በሚገልጽ የኤክስ ፖስት ላይ ስምምነቱን በግለጹ ምክንያት ከፍተኛ ትችት አስተናግዷል።
ፖስቱን ተከትሎም ዋልት ዲስኒን፣ ዋርነር ብሮስ ዲስከቨሪን እና ኤንቢሲ ዩኒቨርሳል ፖረንትኮምካስትን ጨምሮ ትላልቅ የአሜሪካ ኩባንያዎች በኤክስ ወይም በፊት ትዊተር በሚባለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያላቸውን ማስታወቂያ አቁመውታል።
ኃይዋት ሀውስም የመስክ ፖስት ጸረ- ሴማዊነትን የሚያበረታታ ነው ሲል ተችቶታል።
መስክ በበኩሉ ጸረ- ሴማዊነትን እንደሚቃወም እና ኤክስም የጥላቻ ንግግርን እንደማያስተዋውቅ እየተናገረ ነው።
ሰባት ሰምንታትን ያስቆጠረው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት በኳታር አደራዳሪነት በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ጋብ ብሏል።
በትናንትናው እለት ቀደም ሲል የተደረሰውን የአራት ቀን ተኩስ አቁም ስምምነት በሁለት ቀን ተራዝሟል።
ተኩስ አቁሙን ተከትሎ በሀማስ እጅ የነበሩ በርካታ የእስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ እና በእስር ላይ የነበሩ ፍልሴጤማውያን እንዲለቀቁ አስችሏል።