ኢለን መስክ በጋዛ የተቋረጡ ግንኙነቶች በስታርሊንክ እንደሚመለሱ ተናገረ
ስታርሊንክ ከዚህ በፊትም በግጭት ምክንያት ኢንተርኔት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች አገልግሎት ሰጥቷል
የስልክ እና የኢንተርኔት መቋረጥ በጋዛ ያሉ ሰዎች እርስበእርሳቸው እንዳይገናኙ እና ከተቀረው አለም እንዲነጠሉ አድርጓቸዋል ተብሏል
ኢለን መስክ በጋዛ የተቋረጡ ግንኙነቶች በስታርሊንክ እንደሚመለሱ ተናገረ
አሜሪካዊው ቢሊየነር ኢሎን መስክ ቅዳሜ እለት እንደተናገረው የስፔስኤክሱ ስታርሊንክ አለምአቀፍ እውቅና ባላቸው ድርጅቶች በኩል በጋዛ የተቋረጡትን የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ይመልሳል።
የስልክ እና የኢንተርኔት መቋረጥ በጋዛ ያሉ ሰዎች እርስበእርሳቸው እንዳይገናኙ እና ከተቀረው አለም እንዲነጠሉ አድርጓቸዋል ተብሏል።
አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንደገለጹት አርብ እለት የጀመረው የስልክ እና ኢንተርኔት መቋረጥ ተስፋ አስቆራጭ የሆነውን ሁኔታ ያባብሰዋል።
የአገልግሎቱ መቋረጥ የህይወት አድን ስራ እንዳይሰሩ እና ችግር አለበት ቦታ ካሉ ሰራተኞች ጋር ለመገናኘት እክል መፍጠሩን ድርጅቶቹ ገልጸዋል።
ስታርሊንክ ከዚህ በፊትም በግጭት ምክንያት ኢንተርኔት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች አገልግሎት ሰጥቷል።
በፈረንጆቹ 2022 ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ መክፈቷን ተከትሎ የተከሰተውን የአገልግሎት መቋረጥ ለመመለስ ስታርሊንክ ጥቅም ላይ ውሏል።
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በአብላጫ ድሞጽ ቢያጸድቅም ሀማስን ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ የምትለው እስራኤል በተመድ ውሳኔ እንደማትገዛ እና ተኩስም እንደማታቆም ገልጻለች።
ተኩስ እንዲቆም ሲጠይቅ የነበረው ሀማስም እስራኤል የእግረኛ ጦር በማሰለፍ ጋዛ ውስጥ ከገባች በኋላ በመሉ አቅሙ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
በእስራኤል ከበባ ውስጥ ያሉት 2.3 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን ለከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ ተዳርገዋል።