የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ኢለን መስክ የበለጸጉ ሀገራት ልጆችን እንዲወልዱ ጠየቁ
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ኢለን መስክ የበለጸጉ ሀገራት ልጆችን እንዲወልዱ ጠየቁ
አንዳንድ ሀገራት ዜጎቻቸው ልጆችን እንዲወልዱላቸው ማበረታቻዎችን አዘጋጅተዋል
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ኢለን መስክ የበለጸጉ ሀገራት ልጆችን እንዲወልዱ ጠየቁ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባሳለፍነው ዓመት ባወጣው ሪፖርት በ2050 የዓለም ህዝብ ቁጥር 10 ቢሊዮን ገደማ እንደሚደርስ ተንብዮ ነበር፡፡
በዚህ ሪፖርት መሰረት የምድራችን ሀብታሙ የሚባለው አህጉር አውሮፓ የህዝብ ብዛቱ አሁን ካለበት ይቀንሳል ብሏል፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ኢለን መስክ በጣልያን በተካሄደ አንድ የፖለቲካ ፌስቲቫል ላይ አውሮፓዊያን ልጆችን እንዲወልዱ ጠይቀዋል፡፡
የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ባዘጋጁት በዚህ ጉባኤ ላይ የክብር እንግዳ የሆኑት ኢለን መስክ ኢንቨስትመንት እና ባህል ያለ ህዝብ ብዛት አይሳካምም ብለዋል፡፡
38 በመቶ አውሮፓዊያን በቀን ሶስቴ እንደማይመገቡ ተገለጸ
ባህል እና ኢንቨስትመንት በስደተኞች አይሳካም ያሉት ባለጸጋው አውሮፓዊን ልጆችን ሊወልዱ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ጣልያንን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን የበለጸጉ ሀገራት ዜጎቻቸው ቤተሰብ እንዲመሰርቱ እና ልጆችን እንዲወልዱላቸው የተለያዩ ማበረታቻዎችን ዘርግተዋል፡፡
ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጣልያን፣ስፔን፣ ግሪክ እና ሀንጋሪ ዝቅተኛ ዓመታዊ የህጻናት ውልደት ያለባቸው ሀገራት ሲሆኑ ኒጀር፣ አንጎላ፣ ቤኒን እና ኡጋንዳ ደግሞ ከፍተኛ ህጻናት የሚወለድባቸው የዓለማችን ሀገራት ናቸው፡፡
1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት አፍሪካ በ2050 የህዝብ ቁጥሯ ወደ ወደ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንደሚያድግ ይጠበቃል፡፡
አሁን ላይ በህዝብ ብዛት 12ኛ ደረጃ ላይ ያለችው ኢትዮጵያ በ2050 213 ሚሊዮን ህዝብ በመያዝ በህዝብ ብዛት ዘጠነኛዋ የዓለማችን ሀገር እንደምትሆን የተመድ ስነ ህዝብ ፖሊሲ ሪፖርት ትንበያ ያስረዳል፡፡