ኩባንያው ይህን እቅዱን ባሳወቀ በዲቃዎች ውስጥ የአክስዮን ዋጋው ጭማሪ አሳይቷል
ቴስላ ኩባንያ ሹፌር አልባ የታክሲ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማምረት የሚታወቀው ቴስላ ኩባንያ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
የቴስላ ኩባንያ መስራች የሆነው ኢለን መስክ በኤክስ አካውንቱ እንደገለጸው የፊታችን ነሀሴ 8 ላይ ቴስላ የመጀመሪያውን ሮቦት ታክሲ አገልግሎት ይጀምራል ብለዋል፡፡
እንደ ኢለን መስክ ገለጻ ሹፌር አልባ የታክሲ አገልግሎት በተለይም ድካም እና አልኮል የጠጡ ሰዎች ይህን አገልግሎት ይጠቀማሉ ብሏል፡፡
በ2024 ለገበያ የሚቀርቡ አይነግቡ ተሽከርካሪዎች
የኢለን መስክ መልዕክትን ተከትሎ የቴስላ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ በ3 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያሽከረክሩ መኪኖች ወደ አገልግሎት መግባታው ባለ ንብረቶች የሆነ ቦታ ከሚያቆሙት ይልቅ ለተለያዩ አገልግሎቶች ቢልኳቸው እና ቢጠቀሙባቸው የተሸለ ይሆናልም ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ትራንስፖርት ባለስልጣን ሹፌር አልባ ተሽከርካሪዎች ደህንነት አገልግሎት መስጠት ይችላሉ አይችሉም የሚለውን እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ቴስላ ኩባንያ በቀጣዩ የክረምት ወራት በአንጻራዊነት ርካሽ የተባሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ለማቅረብ የነበረውን እቅድ ሰርዣለሁ ብሏል፡፡
የቴስላ ኩባንያ ምርት የሖኑ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የ8 በመቶ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን የቻይና አቻ ኩባንያዎች ፉክክር ለኩባንያው ገቢ መቀነስ ምክንት ሆኗል፡፡