የኢለን መስክ ሀብት 400 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ
ኤክስን ጨምሮ የቴስላ እና ስፔስ ኤክስ ኩባንያ ባለቤት የሆነው ኢለን መስክ ከአሜሪካ ምርጫ በኋላ ሀብቱ አሻቅቧል
ኢለን መስክ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ይሻገራል ተብሏል
የኢለን መስክ ሀብት 400 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ።
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው አሜሪካዊ ቢሊየነር ኢለን መስክ የሀብት መጠኑ በእጅጉ ጨምሮለታል ተብሏል።
እንደ ብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ የኢለን መስክ ሀብት መጠን 400 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
የኢለን መስክ ሀብት መጠን በተለይም ከአንድ ወር በፊት በተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በኋላ ከፍተኛ የሚባል ጭማሪ አሳይቷል።
የምርጫው አሸናፊ ዶናልድ ትራምፕ ኢለን መስክን የአስተዳድራቸው አንድ አካል እንደሚሆን ገልጸዋል።
አሜሪካዊያን በምርጫው ላይ እንዲዳተፉ እና ድምጽ እንዲሰጡ በየቀኑ አንድ ሚሊዮን ዶላር ሲሸልም የነበረ ሲሆን የትራምፕ ዋነኛ ደጋፊም ሆኗል።
ምርጫውን ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕም ኢለን መስክን የመንግስታቸው ውጤታማነት ጉዳዮች ሀላፊ እንደሚያደርጉትም ይፋ አድርገዋል።
ይህን ተከትሎም የኢለን መስክ ንብረት የሆኑት ስፔስ ኤክስ፣ ቴስላ፣ ኤክስ እና ሌሎችም ኩባንያዎች አክስዮን ዋጋቸው ጨምሯል።
በዚህም መሰረት የኢለን መስክ ጠቅላላ ሀብት 400 ቢሊዮን ዶላር በመድረስ በታሪክ ትልቅ ሀብት ያለው ገለሰብ መሆን ችሏል።
ኢለን መስክ በአንድ ወር ውስጥ የሀብት መጠኑ የ20 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ እንዳሳየም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ከአንድ ወር በፊት ፎርብስ ባወጣው ሪፖርት መሰረት በፈረንጆቹ 2027 ላይ የኢለን መስክ ሀብት መጠን አንድ ትሪሊዮን እንደሚደርስ ገልጿል።