ኢለን መስክ ነኝ በሚል 600 ሺህ ዶላር ያጭበረበረው ሰው
ራሱን ኢለን መስክ ነኝ የሚለው ይህ ሰው አንዲት ሴትን በጋራ እንነግድ በሚል እንዳጭበረበረ ተገልጿል
ፖሊስ ግለሰቡን በከባድ ማጭበርበር ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር አውሎታል
ኢለን መስክ ነኝ በሚል 600 ሺህ ዶላር ያጭበረበረው ሰው
በአሜሪካዋ ፍሎሪዳ የሚኖረው ጀፍሪ ሞይኒሃን የኣለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው ኢለን መስክ ነኝ በሚል ነበር አንድ ስሟ ያልተጠቀሰች ሴት የተዋወቀው፡፡
በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የተደረገው ይህ ትውውቅ ቀስ በቀስ ወደ መተማመን ተቀይሮ ስልክ መደዋወል፣ መልዕክት መላላክ ይደርሳል፡፡
ከአንድ ዓመት ትውውቅ በኋላ ህ ወዳጅነት ለምን አብረን አንሰራም ወደሚል ትብብር ተቀይሯል የተባለ ሲሆን እንስቷ እያወራት ያለው ሰው ኢለን መስክ መሆኑን እርግጠኝ ትሆናለች፡፡
በጋራ ለመስራት በተስማሙት መሰረትም በተለያዩ ጊዜያት የገንዘብ ዝውውር ወደ ኢለን መስክ ነኝ ወደሚለው ሰው ትልካለች፡፡
አሜሪካን 50 ቢሊየን ዶላር ያሳጡት አፍሪካውያን ዲጂታል አጭበርባሪዎች
በተደረገው ስምምነት መሰረትም በአጠቃላይ 600 ሺህ ዶላር ገንዘብ ኢንቨስት በማድረግ 55 ሚሊዮን ዶላር ትርፍ እንደምታገኝ ኢለን መስክ ነኝ የሚለው ሰው አሳምኗታል፡፡
ይሁንና ይህ ሁሉ ሌብነት መሆኑን የደረሰበት ፖሊስ ኢለን መስክ ነኝ የሚለውን ሰው በያዝነው ሳምንት ሰኞ ዕለት ከመኖሪያ ቤቱ በቁጥጥር ስር አውሎታል፡፡
በግለሰቡ የባንክ ሂሳብ ውስጥ 250 ሺህ ዶላር ብቻ የተገኘ ሲሆን ቀሪው የት እንደገባ ምርመራ በመደረግ ለይ እንደሆነ ኒዮርክ ፖስት ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ሰው በአካውንቱ ውስጥ የተገኘው 250 ሺህ ዶላር ገንዘብ የፍቅረኛው እንደሆነ ተናግሯል፡፡
ስለ ፍቅረኛው የተጠየቀው ይህ ሰውም እስካሁን በአካል አግኝቷል እንደማያውቅ እና በኢንተርኔት አማካኝነት ብቻ እንደሚያወሩ መናገሩን ተከትሎ ግለሰቡ በሌላ አጭበርባሪ ሳይታለል እንዳልቀረ የተገለጸ ሲሆን ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡