እየሱስ ነኝ በሚል 300 ሺህ ዩሮ የተቀበለው አጭበርባሪ ተያዘ
ግለሰቡ አንድ በእድሜ የገፉ አዛውንትን እየሱስ ነኝ በሚል ገንዘባቸውን አጭበርብሮ እንደወሰደ ተገልጿል
ግለሰቡ አዛውንቷን በገነት ውስጥ ለምታሳልፊው ህይወት ወጪ ይሆንሻል በሚል ገንዘቡን እሱ ጋር እንድታስቀምጥ አድርጓል ተብሏል
እየሱስ ነኝ በሚል 300 ሺህ ዩሮ የተቀበለው አጭበርባሪ ተያዘ።
በሀገረ ስፔን እኔ እየሱስ ነኝ በሚል አንድ አዛውንትን በማጭበርበር ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተቀበለ ተገልጿል።
ግለሰቡ አዛውንቷን በገነት ህይወትሽ ለሚያስፈልጉሽ አንዳንድ ነገሮች በከፍተኛ ወለድ ያላትን ገንዘብ እሱ ባዘጋጀው አነስተኛ እቃ ውስጥ እንድትቆጥብ እድርጋል ተብሏል።
እስፔራንዛ የተሳኙት እኝህ አዛውንትም ከእየሱስ እንደተደወለላት፣ ገነት እንደምትገባ እና ገንዘቧን እንድትቆጥብ እንደተነገራት ለቤተሰቦቿ መናገራም ተገልጿል።
አዛውንቷ ሴትዮም እራሱን እየሱስ ነኝ በሚለው ግለሰብ በመታለል ላለፉት ስድስት ዓመታት ያላትን ገንዘብ ሁሉ እያወጣች ሰጥታለች ተብሏል።
ግለሰቧ ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ እየሱስ ነኝ ብሎ ለነገራቸው ግለሰብ ገንዘባን ስትሰጥ ቆይታለች ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግባል።
አዛውንቷ ከእሷ በተጨማሪም ለሴት ልጇም ቅዱስ እንደሆነች ስትነግራት ቆይታለች የተባለ ሲሆን ልጅቷ ግን እንደ እናቷ አለመታለሏ ተገልጿል።
በገነት ውስጥ የተንደላቀቀ ህይወት ለማሳለፍ ቁጠባ ጀምሬያለሁ ያለችው ይህች ግለሰብም በሁለት ባንኮች ውስጥ የነበራትን ገንዘብ ሳይቀር እያወጣች እየሱስ ነኝ የሚለው ሰው ባዘጋጀላት ማጠራቀሚያ እቃ ውስጥ ስታስቀምጥ እንደቆየችም ገልጻለች።
እራሱን እየሱስ ነኝ በሚል ማጭበርበሩ የተደረሰበት ግለሰብም ወንጀል እንዳልፈጸመ ቢከራከርም የሀገሪቱ መርማሪ ባደረጋቸው የስልክ እና ሌላሎች ምርመራዎች ጥፋተኛ ኮኖ ተገኝቷል ተብሏል።
የስፔን ፍርድ ቤት ግለሰቡ የአዛውንቷን በእድሜ መግፋት እና የማሰላሰል አቅምን በመጠቀም በማጭበትበር ወንጀል የስምንት ዓመት እስር ተላልፎበታል።