ኢለን መስክ የዓለም ቁጥር አንድ ባለጸጋነት ደረጃውን ተነጠቀ
ላለፉት ሶስት ዓመታት የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የነበረውን ኢለን መስክ የተካው ሰው ማን ነው?
ኢለን መስክ በአንድ ቀን 18 ቢሊዮን ዶላር ገቢውን አጥቷል
በአንድ ቀን 18 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ያስመዘገበው ኢለን መስክ የዓለም ቁጥር አንድ የዓለም ባለጸጋ ደረጃውን ተነጠቀ፡፡
ላለፉት ሶስት ዓመታት የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የነበሩት ኢለን መስክ ደረጃቸውን እንደተነጠቁ ፎርብስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ኢለን መስክ በአንድ ቀን የተጣራ 8 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ አስመዝግቧል የተባለ ሲሆን የተጣራ ሀብቱም 204 ቢሊዮን ዶላር ሆኗል፡፡
በፋሺን ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራው ፈረንሳዊው በርናርድ አርናልት በ207 ቢሊዮን ዶላር የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነ ሲሆን በአንድ ሳምንት ውስጥ የ23 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል ተብሏል፡፡
ኢለን መስክ ኪሳራ ሊያስመዘግብ የቻለው የድርጅቱ ቴስላ ኩባንያ የፋይናንስ ሪፖርት የ15 በመቶ ቅናሽ አሳየ የሚለው ሪፖርት ይፋ መደረጉን ተከትሎ የድርጅቶቹ አክስዮን ዋጋ ሊቀንስ ችሏል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ጉዳት መቀነሱ እና የፋሺን ኢንዱስትሪው ወደ ቀድሞ ቦታው መመለሱ ለአርናልት ገቢ መጨመር ዋነኛ ምክንያት ነው የተባለ ሲሆን በተጠናቀቀው የ2023 ዓመት ብቻ 86 ቢሊዮን ገቢ ማግኘቱ ተገልጿል፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ ሴት ባለጸጋ ፍራንሶይዝ መየርስ ማን ናቸው?
ፈረንሳይ የ2024 ኦሎምፒክ አዘጋጅ ሀገር መሆኗ ለበርናርድ ኩባንያዎች የመዋቢያ እና ፋሺን ምርቶች ተጨማሪ የገበያ እድል የሚፈጥሩ በመሆኑ ገቢያቸው እንደሚያድግም ይጠበቃል፡፡
በተያዘው የ2024 ዓመት ለአውቶሞቢል ኢንዱስትሪ ፈታኝ ዓመት ይሆናል መባሉን ተከትሎ የኢለን መስኩ ቴስላ ኩባንያ ትርፉ ሊቀንስ ይችላል ተብሏል፡፡
የምርት ግብዓት ዋጋ መናር፣ የቻይና ኩባንያዎች ተጽዕኖ መጨመር እና የዓለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ደግሞ ይህን ኢንዱስሪ ይፈትናሉ የተባሉ ጉዳዮች ናቸው፡፡