ፈረንሳዊቷ ይህች የዓለማችን ቁጥር አንድ የናጠጡ ሀብታም እንስት የመዋቢያ ምርቶች እና ፋሽን ነጋዴ ናት
የዓለማችን ቁጥር አንድ ሴት ባለጸጋ ፍራንሲስ መየርስ ማን ናቸው?
ሙሉ ስማቸው ፍራንሶይዝ ቤትንኮርት መየርስ የባላሉ፡፡ ፈረንሳዊት ሲሆኑ የሀብት መጠናቸው 90 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡
ዓለም አቀፍ ብራንድ ያላቸው የመዋቢያ እና ፈሽን ኢንዱትሪ ዘርፍ ንግድ የተሰማሩ ሲሆን ይህ ንግድ ከቤተሰባቸው ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣም ተገልጿል፡፡
ለኦሪል የተሰኘ ኩባንያ ወራሽ በመሆን የፋሽን ኢንዱስትሪውን የተቀላቀሉት የ70 ዓመቷ ይህች እንስት አሁን ላይ ቁጥር አንድ የዓለማችን ባለጸጋ እንስት ሆነዋል፡፡
የሁለት ልጆች እናት የሆኑት ፍራንሶይዝ መየርስ በዓለማችን ካሉ አጠቃላይ ቢሊየነሮች ውስጥ በ12ኛ ደረጃ ሲቀመጡ ትርፋቸው በተጠናቀቀው 2023 ዓመት ወደ 35 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገልጿል፡፡
የ2023 የአለም 10 የሀብት ባለጸጋዎች (ቢሊየነሮች)
በዓመት 524 ቢሊዮን ግብይት የሚፈጸምበት የዓለም ፋሽን ኢንዱስትሪ ከኮሮና ቫይረስ በኋላ ዳግም በመነቃቃት ላይ መሆኑ እንስቷ ተጨማሪ ሀብት እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡
ለኦሬል የተሰኘው ይህ ኩባንያቸው በ2023 ዓመት ብቻ የሽያጭ መጠኑ 38 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን የአውስትራሊውን ኤሶፕ ኩባንያንም በ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ጠቅልሎታል፡፡
ለኦሪል የተሰኘው ይህ ፍራንሶይዝ መየርስ ኩባንያ አርማኒ፣ ጂዮርጂዮ፣ ማይቤሊን ፣ሴንት ላውሬንት እና ሌሎችም ብራንዶችን በባለቤትነት ይዟል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍራንሶይዝ መየርስ በመቀጠል አሜሪካዊያኑ ጁሊያ ኮች 59 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም የወልማርት ባለቤቷ አሊስ ዋልተን 56 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በመያዝ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሴት ባለጸጋዎች ናቸው፡፡
ከወንዶች ደግሞ ኢለን መስክ 245 ቢሊዮን ዶላር፣ በርናርድ አርናልት 196 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ጄፍ ቤዞፍ 168 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በመያዝ የዓለማችን ቀዳሚ ባለጸጋዎች ናቸው፡፡