ኢኮኖሚ
የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊየነር ከሶስት ዓመት በኋላ ይታወቃል ተባለ
የትሪሊየነር ደረጃን ይይዛሉ ከተባሉ 15 ባለጸጋዎች ውስጥ 10ሩ አሜሪካዊን እንደሚሆኑ ተገልጿል
ኢለን መስክ በ2027 የሀብት መጠኑ ወደ ትሪየነርነት ይሸጋገራል ተብሏል
በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች በየዓመቱ ከፍተኛ የተባለውን ትርፍ በማግኘት ላይ ሲሆኑ ዓለማችን ካሏቸው ቀዳሚ ባለጸጋዎች መካከልም ዋነኞቹ ናቸው፡፡
236 ቢሊዮን ዩሮ ሀብት በመያዝ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው ኢለን መስክ በ2027 በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ትሪሊየነር ደረጃን እንደሚይዝ የብሉምበርግ ቢሊየነር ሪፖርት ትንበያ ያስረዳል፡፡
እንደ ትንበያው ከሆነ ከኢለን መስክ በመቀጠል የህንዱ ጓታም አዳኒ በ2028 ለይ ሁለተኛው ትሪሊየነር እንደሚባልም ተገልጿል፡፡
የ61 ዓመቱ እና የኒቪዳ ኩባንያ ባለቤቱ ጄሰን ሁዋንግ በ2028 የሀብት መጠኑ ትሪሊየን ይገባል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ 112 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ባለቤት ነው፡፡
በአጠቃላይ እስከ ፈረንጆቹ 2037 ዓመት ድረስ 15 ዓለማችን በላጸጋዎች የሀብት መጠናቸው ከቢሊዮን ወደ ትሪሊየነርነት እንደሚያድግ ተገልጿል፡፡
በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ሀብት መጠናቸው ወደ ትሪሊየነርነት ከሚገባላቸው ባለጸጋዎች መካከል አስሩ አሜሪካዊያን ሲሆኑ ሁለት ህንዳዊያን እንዲሁም ኢንዶኔዢያ ፈረንሳይ እና ቻይና ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ትሪሊየነር ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡