ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለምክር ቤቱ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል
አሜሪካ ብርቱ የደህንነት ስጋት እንደተጋረጠባት ገለጸች፡፡
የአሜሪካ ምክር ቤት የደህንነት ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ማይክ ተርነር አሜሪካ ብርቱ የደህንነት ስጋትአጋጥሟታል ብለዋል፡፡
ሊቀመንበሩ አክለውም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ምክር ቤቱ መጥተው ስጋቶችን ግልጽ እንዲያደርጉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
አሜሪካ ያጋጠማት የደህንነት ስጋት ከሩሲያ ጋር የተገናኘ ነው የተባለ ሲሆን ፕሬዝዳንት ባይደን በስጋቱ ዙሪያ ግልጽ መረጃ ለህዝብ እና ለወዳጆቻችን ካብራሩ በኋላ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎችም ፍንጭ ሊሰጡ ይገባል ተብሏል፡፡
ማይክ ተርነር ከዚህ በላይ ጉዳዩን ግልጽ ማድረግ እንደማይፈልጉ የተናገሩ ሲሆን ዘግይቶ በወጣው መረጃ መሰረት ሩሲያ በጠፈር ላይ ልታካሂደው ያሰበችው እቅድ የአሜሪካንን ጥቅም የሚጎዳ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የደህንነት አማካሪ ጃክ ሱልቪያን በበኩላቸው በማይክ ተርነር አስተያየት መገረማቸውን ገልጸው እሳቸውን ጨምሮ የመከላከያ እና የደህንነት ባለሙያዎች ጋር በመሆን ከምክር ቤት አባላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ለመወያየት ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡
“በዚህ ጉዳይ ከዚህ በላይ እንድል ስልጣን የለኝም፣ በያዝነው ቀጠሮ መሰረት ከማይክ ተርነር ጋር እንወያያለን” ያሉት ሱልቪያን ስምንት አባላት ካሉት እና ከሀገሪቱ ምክር ቤት ተመራጮች ጋር እንደሚወያዩበትም አስታውቀዋል፡፡
የ81 አመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የቲክቶክ አካውንት ከፈቱ
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዚህ በፊት ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር ካደረገቻቸው የጠፈር ስምምነቶች ልትወጣ እንደምትችል አስጠንቅቀው ነበር፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ሩሲያ 2 ነጥብ 3 ቶን ክብደት ያላቸው ቁሳቁሶችን ወደ ህዋ ያጓጓዘች ሲሆን እነዚህ ቁሳቁሶች በጠፈር ላይ ያሉ የሩሲያ ሳተላይቶችን ለማደስ ይውላሉ ተብሏል፡፡