የኤምሬትስ ባለስልጣናት በሞልዶቫን ዜጋ ግድያ የፈፀሙትን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
ግድያ የተፈጸመበት ዝቪ ኮጋን የሞልዶቫ ዜግነት ያለው መሆኑን ወደ አረብ ኢሚሬትስ ከገባበት መታወቂያ ሰነድ መረዳት ተችሏል
ክዝቪ ኮጋ ግድያ ጋር በተያያዘ ሶስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአረብ ኢምሬትስ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር እታውቋል
የኤምሬትስ ባለስልጣናት በሞልዶቫን ዜጋ በሆነው ዝቪ ኮጋን ላይ ግድያ የፈፀሙትን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የአረብ ኢምሬትስ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአረብ ኢምሬትስ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ማሻውን ባወጣው መግለጫ፤ በሀገሪቱ ውስጥ ተገድሏል የተባለው ዝቪ ኮጋን የሞልዶቫ ዜግነት ያለው መሆኑን ወደ አረብ ኢሚሬትስ ከገባበት መታወቂያ ሰነድ መረዳት ተችሏል ብሏል።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው የጠፋ ሰው ሪፖርት ከተጎጂው ቤተሰብ ሲደርሰው፣ ልዩ የፍለጋ እና የምርመራ ቡድን በፍጥነት በማዋቀር ወደ ስራ መግባቱን አብራርቷል።
ይህም የተጎጂውን አስከሬን ፈልጎ ማግኘት፣ ወንጀለኞችን መለየት እና ማሰር እንዲሁም አስፈላጊ የህግ ሂደቶችን እንዲጀመሩ እንዳስቻለም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ስለ ግድያ ወንጀሉ ሙሉ መረጃ የምርመራው ውጤት ሲጠናቀቅ በዝርዝር እንደሚገለጽም ነው የተብራራው።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ተቋማቱ የዜጎችን፣ የነዋሪዎቿን እና የጎብኝዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳላቸው ሚኒስቴሩ አረጋግጧል።
የሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መሰረታዊ የሆኑትን የደህንነት ከፍተኛ ደረጃዎችን እንደሚጠብቅ አጉልቶ ማሳየቱንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው።
ሚኒስቴሩ የህብረተሰቡን መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥሉ እርምጃዎችን እና ሙከራዎችን በቆራጥነት መልስ ለመስጠት ሁሉንም የህግ ስልጣን እንደሚጠቀም አሳስቧል።