ተከሳሾቹ ወደ አቡ ዳቢ የተዛወሩት ተከሳሾቹ ጸጥታ ለማደፍረስ የሚውል ሚስጥራዊ ድርጅት በማቋቋም እና በሀገሪቱ ላይ የሽብር ተግባር በመፈጸም ክስ እንዲመሰረትባቸው ነው
አረብ ኢምሬትስ 84 ግለሰቦችን ሚስጥራዊ ድርጅት በማቋቋም እና በሽበር ልትስ ነው።
የአረብ ኢምሬትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ሀማድ ሰይፍ አል ሻምሲ በአብዛኛው በኢምሬትስ በሽብር የተፈረጀው 'የሙስሊም ብራዘርሁድ' አባል የሆኑ 84 ግለሰቦች ወደ አቡ ዳቢ የፌደራል ፍርድቤት እንዲዛወሩ አዘዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ወደ አቡ ዳቢው የሴኩሪቲ ፍርድ ቤት እንዳዛወሩ ትዕዛዝ ያስተላለፉት፣ ተከሳሾቹ ጸጥታ ለማደፍረስ የሚውል ሚስጥራዊ ድርጅት በማቋቋም እና በሀገሪቱ ላይ የሽብር ተግባር በመፈጸም ክስ እንዲመሰረትባቸው ነው።
ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን መረጃ አስተባብለዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባገኘው መረጃ መሰረት ወንጀሉን መመርመሩን እና ለእያንዳንዱ ተከሳሽ የህግ ባለሙያ መመደቡን አስታውቋል።
ስድስት ወራት በፈጀ ምርመራ እና ጥናት የወንጀሉ ዝርዝር ከታወቀ እና በቂ መረጃ ከተገኘ በኋላ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ተከሳሾቹን ወደ አቡ ዳቢው የስቴት ሴኩሪቲ ፍርድ ቤት አስተላልፏቸዋል።
ተከላከይ ጠበቃ ማቆም ላልቻሉት ተከሳሾች ጠበቃ ተመድቦ፣ የምስክሮችን ቃል እየሰማ ነው።