የወቅቱ የሐገሪቱ ፕሬዝዳንት ፓርቲ አብላጫ ወንበሩን ለተቀናቃኝ ፓርቲ አሳልፎ ሰጥቷል ተብሏል
የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓርቲ 245 የፓርላማ መቀመጫዎችን አጣ፡፡
ከአንድ ወር በፊት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አድርጋ ኢማኑኤል ማክሮንን ለሁለተኛ ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አድርጋ የመረጠችው ፈረንሳይ አሁን ደግሞ የሕግ አውጭዎች ምክር ቤት ምርጫ አካሂዳለች፡፡
በዚህ ምርጫ ላይ የፕሬዝዳንት ማክሮን ፓርቲ በምክር ቤቱ የአብላጫ ወንበርን ለተቀናቃኛቸው ቀኝ እና ግራ ዘመም ፓርቲዎች ህብረት አሳልፈው መስጠታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓርቲ 245 የህግ አውጪ ምክር ቤት መቀመጫዎችን አጥቷል፡፡
የፈረንሳይ የሕግ አውጪ ምክር ቤት 289 መቀመጫ ያለው ሲሆን ተቃዋሚዎች 245 መቀመጫዎችን ማሸነፍ ችለዋል ተብሏል፡፡
በዚህ ምርጫ የግራ ዘመም ፓርቲዎች ህብረት 131 የምክር ቤት መቀመጫዎችን ሲያሸንፉ በማሪን ለፐን የሚመራው ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች ህብረት ደግሞ 89 መቀመጫዎችን እንዳሸነፉ ተገልጿል፡፡
በፈረንሳይ በሁሉም ቦታዎች በተካሄደው በዚህ ምርጫ የመራጭነት ካርድ ከወሰዱት ውስጥ ድምጽ የሰጡት ከ50 በመቶ በታች ያህሉ ብቻ ሲሆኑ ይህም ከአምስት ዓመት በፊት በተካሄደው የ2017 ምርጫ ጋር ሲነጻጸር አንጻራዊ መሻሻል ማሳየቱን ዘገባው አክሏል፡፡
የምርጫውን ውጤት ተከትሎም በስልጣን ላይ ያለው የፕሬዝዳንት ማክሮን ፓርቲ በቀጣይ ስልጣን ሙሉ ለሙሉ እንደሚያጣ ተጠቁሟል፡፡