ኢማኑዌል ማክሮን፤ የዩክሬን ወደ አውሮፓ ህብረት የመቀላቀል ጉዳይ “አስርት ዓመታት ሊፈጅ ይችላል” አሉ
ማክሮን የዩክሬን ጉዳይ ለማፋጠን ከአውሮፓ ህብረት በተጨማሪ ሌላ“አቻ አውሮፓዊ የፖለቲካ ማህበረሰብ” ሊቋቋም ይገባልም ብሏል
ዩክሬን ወደ አውሮፓ ህብረት የመቀላቀል ጥያቄ ያቀረበችው ጦርነቱ ከተጀመረ ከአራት ቀናት በኋላ እንደነበር ይታወሳል
የዩክሬን ወደ አውሮፓ ህብረት የመቀላቀል ጉዳይ አስርት ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን ተናገሩ፡፡
ማክሮን ይህን ያሉት፤ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሰላ ቮን ደር ለየን የህብረቱ በላይ አካል በዩክሬን ጉዳይ ላይ የመጀመሪያ አስተያየቱን እንደሚሰጥ መናገራቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ፕሬዝዳንቱ በስትራስበርግ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ባሰሙት ንግግር እንዳሉት ከሆነ፤ አሁን ባለው የህብረቱ አሰራር የዩክሬን ጉዳይ ጊዜ እንዲፈጅ የሚያደርግ ነው መሆኑ ተናግሯል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በሰጡት አስተያየት "ወደ ህብረቱ የመቀላቀል ሂደቱና አሰራሩ ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል ሁላችን አናውቃለን" ብሏል።
"መስፈርቱን ዝቅ ለማድግ ካልወሰንን እውነታው ይህ ነው ፤ ለአውሮፓ አንድነት ስንል ደግመን ማሰብ አለብን " ሲሉም አክሏል ማክሮን።
ማክሮን፤ የዩክሬን አባልነትን ለማቀላጠፍ በሚል የህብረቱ መስፈርቶችን ከመድፈቅ ይልቅ ከአውሮፓ ህብረት በላይ የሆነና ብሪታንያን ሊያካትት የሚችል “አቻ አውሮፓዊ የፖለቲካ ማህበረሰብ” ማቋቋም እንደ አማራጭ ማየቱ ተገቢ መሆኑም ምክረ-ሃሳብ አቅርቧል፡፡
"ይህ በጂኦግራፊ ከአውሮፓ ህብረት ውጭ ያሉትን ሀገራት ለመያዝ የምንችልበትና እሴቶቻችንን ለማካፈል የምንችልበት መንገድ ነው"ም ብሏል ማክሮን፡፡
የዩክሬን ባለስልጣነት በትናንትናው እለት እንደገለጹት ከሆነ፤የዩክሬን ወደ አውሮፓ ህብረት መቀላቀልን በተመለከት ለሁለተኛ ጊዜ የአብየቱታ ጥሪ ወደ ብራስለስ ቀርቧል፡፡
ዩክሬን ወደ አውሮፓ ህብረት የመቀላቀል ጥያቄ ያቀረበችው፤ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ከአራት ቀናት በኋላ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
ሩሰያ ፤ በዩክሬን ምስራቀዊ ክፍል የሚገኘውን የዶምባስ ግዛት ለመቆጠጠር መጠነ ሰፊ ጥቃት እየሰነዘረች ቢሆንም፤ ከዩክሬን ኃይሎች ከባድ የሚባል የጸረ-ማጥቃት እርምጃዎች እያስተናገደች መሆኗ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ዚ-ኢኮነሚክ ታይምስ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ወታደራዊ መኮንንን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው ከሆነ ፤ሩሲያ በዩክሬን ምድር እያደረገችው ያለውን ጦርነት እንዳሰበቸው አልሆነላትም ፡፡
እንደ ዶምባሳ ሁሉ ሉሃንስክ ሌላኛዋ ከባድ የሚባል ጦርነት እየተካሄደባት የምትገኝ የዩክሬን ግዛት ናት፡፡