ማክሮን ተቀናቃኛቸውን ማሪን ለ ፐን በ58.2 በመቶ ለ 41.8 በመቶ በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ተነግሯል
ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመረጡ።
በፈረንሳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሁለተኛ ዙር ድምጽ የመስጠት ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል።
ኢማኑኤል ማክሮን ከ20 ዓመታት ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ ፈረንሳይን ለመምራት የተመረጡ የመጀመሪያው መሪ መሆን ችለዋል።
በሁለተኛ ዙር የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ግራ ዘመሙዋ ማሪን ለ ፐን ተፎካክረዋል።
በዛሬው ምርጫም ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተቀናቃኛቸው ማሪን ሊ ፐንን በ58.2 በመቶ ለ 41.8 በመቶ በሆነ ውጤት ማሸነፋቸውን ፍራንስ24 ዘግቧል።