ከአዳዲሶቹ አገልግሎቶች ውስጥም በተለያዩ ቋንቋ የሚመጡልን መልእክቶችን መተርጎም ይገኝበታል
የመልእክት መላላኪያ የሆነው ቴሌግራም በአዲሱ የፈረንጆኑ ዓመት 2022 አዳዲስ አገልግሎቶች በመተግሪያው ላይ ማካተቱን አስታወቀ።
ቴሌግራም በቅርቡ ይፋ ባደረገው 8.4 ማሻሻያው ላይ አዳዲሶቹን ይዘቶች ይዞ የቀረበ ሲሆን፤ ማሻሻያው አንድሮይድም ይሁን አይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለሚጠቀሙ ስልኮች እንደሚያገለግልም ተነግሯል።
አዳዲሶቹ የቴሌግራም ይዘቶች
ለተላኩልን መልስክቶች ስሜታችንን ለመግለፅ የሚያስችሉ ኢሞጂዎች
ከዚህ ቀደም የተላኩለን መልእክቶች ላይ ስሜታችንን ለማንጸባረቅ (message reactions) ለማደረግ የግድ የጽህፉ መላኪያ ውስጥ በመግባት ለብቻ የሚላክ ነበር።
አሁን ባደረገው ማሻሻያ ግን ሪያክት ማድረጊያ ኢሞጂዎች ልክ እንደ ሌሎች የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከመልእክቱ ጎን የሚመጣ መሆኑም ታውቋል።
ኢሞጂዎቹ ውስጥም የአውራ ጣት ወደ ላይ እና ወደታች የሚያሳይ፣ ልብ ቅርጽ እና በግርምት ያፈጠጠ አይን ኢሞጂዎች እንደሚገኙበት ተነግሯል።
በተጨማሪም መልእከቱን ሁለት ጊዜ በመንካት ብቻ በፍጥነት ሪያክት ማድረጊያ መንገድ በአዲሱ ማሻሻያ ላይ እንደተጨመረም ታውቋል።
መልእክት መተርጎም
ቴሌግራም ይፋ ያደረገው ሌላኛው አገልግሎት መልእክተ መተርጎም ሲሆን፤ ይህም በሌላ ቋንቋ የተላከልንን መልእክት እኛ ወደምንረዳው ቋንቋ ለመተርጎም የሚያስችል ነው ።
ይህ የትርጉም አገልግሎት በሁሉም የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲሆን፤ ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች ደግሞ አይ.ኦ.ኤስ 15 ላይ ነው የሚሰራው ተብሏል።
ይህንን አገልግሎት ለማግኘትም በስልካችን ላይ ወይም ኮምፒውተራችን ላይ ያለው ቴሌግራማችንን በመክፈት ሴቲንግ ውስጥ ከገባን በኋላ ቋንቋ የሚያስመርጠው ውስጥ በመግባት “Language” የሚለውን ከከፈትን በኋላ አገልግሎቱ የሚጀምር መሆኑ ታውቋል።