ባለፈው እሁድ በኪሊማንጃሮ ተራራ ላይ የተነሳው እሳት 28 ኪሜ ስኩየር የሚሸፍን ደን አውድሟል ተብሏል
ባለፈው እሁድ በኪሊማንጃሮ ተራራ ላይ የተነሳው እሳት 28 ኪሜ ስኩየር የሚሸፍን ደን አውድሟል ተብሏል
በታንዛኒያ መንግስት በእሳት ማጥፋት ስራ የተሰማሩትን ለመርዳት ሄሊኮፕተርና አውሮፕላኖችን ከላከ በኋላ ከአፍሪካው ትልቅ በሆነው የኪሊማንጃሮ ተራራ ላይ የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡
ባለፈው እሁድ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ከ500 በላይ በጎ ፈቃደኞች መሳተፋቸውን መንግስት አስታውቋል፡፡
የታንዛኒያ የቱሪዝምና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ሀሚሲ ኪግዋንጋላ እንደተናገሩት በተራራው ላይ የነበረው እሳት በአብዛኛው በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
“ለህዝቡ ማለት የምንፈልገው በኪማንጃሮ ተራራ ላይ ተነሳውን እሳት ለማጥፋት የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው፤ ነገርግን እሳቱ በአብዛኛው በቁጥጥር ስር እየዋል ነው “
እሳቱ የተከሰተው ከፍተኛ ቦታ ላይ መሆኑና ንፋሱ እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት አክብደውታል፡፡
የአውሮፓውያን ተራራ ወጭዎች ካምፕ እኩለ ሌሊት አካባቢ በእሳቱ ወድሟል፡፡ ሚኒስትሩ እንደገለጹት የቱሪዝም እንቅስቃሴው በእሳት አልተጎዳም ተብሏል፡፡ እሳቱ በኪሊማንጃሮ ደቡባዊ ክፍል ባለፈው እሁድ ነበር የተነሳው፡፡
እንደ ሚኒስትሩ ከሆነ እሳቱ እስካሁን 28 ኪሜ ስኩየር የሚሸፍን የደን ክፍል አውድሟል፡፡ የእሳቱ መነሻ እስካሁን አልታወቀም፡፡