በእንግሊዝ በርካታ ተጫዋቾች በኮሮና ቫይረስ በመያዛቸው ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን ለይቶ ማቆያ እያስገቡ ነው
በእንግሊዝ በርካታ ተጫዋቾች በኮሮና ቫይረስ በመያዛቸው ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን ለይቶ ማቆያ እያስገቡ ነው
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ዛሬ የጣልያንና የስፔን ሊጎች እጣ ገጥሞታል፡፡
ለዚህ ደግሞ ምክኒያቱ የተለያዩ ክለቦች ተጫዋቾች እና የአርሰናል አሰልጣኝ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡ ነው፡፡
የአርሰናል አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ
አርቴታ በቫይረሱ መያዙ በመረጋገጡ አርሰናል ከ ብራይተን ጋር ነገ ያደርጉት የነበረው ጨዋታ ተራዝሟል።
"መጥፎ ስሜት ሲሰማኝ ነበር ተመርምሬ በቫይረሱ መያዜን ያረጋገጥኩት" ያለው አርቴታ "በቅርቡ ወደ ስራዬ እንደምመለስ አምናለሁ" ብሏል።
መድፈኞቹ የልምምድ ሜዳቸውን የዘጉ ሲሆን ከአርቴታ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው አባላት ራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ ተደርጓል።
የቼልሲ ሙሉ ስኳድ አባላት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለይቶ ማቆያ ገቡ
የክለቡ የክንፍ መስመር ተጫዋች ካሉም ሁድሰን ኦዶይ በኮሮና ቫይረስ መያዙ መረጋገጡን ተከትሎ የክለቡ ሙሉ ስኳድ ለይቶ ማቆያ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ሁድሰን በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝና በቅርቡ ወደ ልምምድ የመመለስ ሀሳብ እንዳለው ክለቡ አስታውቋል፡፡
ኤቨርተን
ኤቨርተንም አንድ ተጫዋቹ የቫይረሱን ምልክት ማሳየቱን ተከትሎ ተጫዋቾቹና የቡድኑ አባላት ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ወስኗል፡፡ በርካታ የዋትፎርድ እና የሌይሲስተር ተጫዋቾችም ህመም እየተሰማቸው እንደሚገኝ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ልምምድ ማቋረጣቸውን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡
የፕሪሚየር ሊግ ባለስልጣናት በሊጉ ቀጣይ እጣ ፋንታ ላይ ለመወሰን ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ሊጉ ቢያንስ እስከ መጋቢት 25/2012 ዓ.ም እንዲቋረጥ ወስነዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። በእንግሊዝና ስኮትላንድ አጠቃላይ የእግር ኳስ ውድድሮች እንዲቋረጡም ተወስወኗል፡፡
የተለያዩ ምንጮችን ለዘገባው በዋቢነት ተጠቅመናል፡፡