ዩኤኢ በግጭቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ሰዎች የ5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እሰጣለሁ ብላለች
ዩኤኢ በግጭቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ሰዎች የ5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እሰጣለሁ ብላለች
በአፍሪካ ቀንድና በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት መከበርና የኢትዮጵያ አንድነት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች(ዩኤኢ) አስታውቃለች፡፡
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት መከበር እንዳለበትና አሁን የተጀመረው ውጊያ መቆም እንዳለበት አስታውቋል፡፡
ሚኒስትሩ ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት መከበር በአፍሪካ ቀንድ ለሚኖረው ሰላምና መረጋጋት ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡
ዩኤኢ አሁን ላይ እየተካሄደ ያለው ውጊያ እንዲቆምና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በአፍሪካ በተለይም በቀጣናው ካሉ አጋሮቿ ጋር መምከሯን አስታውቃለች፡፡
የማዕከላዊ መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት መሪዎች እየተካሄደ ያለውን ውጊያ በማቆም ወደ ንግግር መመለስ አለባቸው ስትል ነው ዩኤኢ የገለጸችው፡፡የኢትዮጵያ መንግስት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈጸሙ የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንዲጀመር ያዘዘው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ነበር፡፡
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት የሚከለክለውን አለምአቀፍ ህግ ማክበር እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ዩኤኢ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የሚፈናቀሉ ሰዎች በተለይም የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ እንደሚየሳስባት ገልጻለች፡፡ ዩኤኢ በአለም አቀፍ የምግብ ፕሮግራም በኩል በግጭቱ ምክንያት ለተሰደዱትና የሰብአዊ እርዳት ለሚያስፈልጋቸው የሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥም ሚኒስትር አስውቀዋል፡፡