“መቀሌን በታንክ ለመክበብ ከሚያስችል ውጊያ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን”- መከላከያ
ህብረተሰቡ በውስጡ የተደበቀውን ኃይል “የግድ ማራቅ ውጣልኝ አታስጨርሰኝ” ማለት አለበት
ጊዜው “መቀሌ ያለው ህዝባችን ከከባድ መሳሪያ ጥቃት ራሱን እንዲታደግ ጥሪ የሚተላለፍበት” ነው
“መቀሌን በታንክ ለመክበብ ከሚያስችል ውጊያ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን”
በተለያዩ ግንባሮች ከህወሓት ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት ጋር እየተዋጋ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ ያለው የመከላከያ ሰራዊት ከከተማዋ በ70 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡
ትናንት ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ በራያ ግንባር የሚደረገው ዘመቻ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል ያሉት የግንባሩ የሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ የተራራ ውጊያዎችን ጨርሰን ቁልቁል ከምን ወርድበት የውጊያ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
“ከእንግዲህ ያለው ውጊያ የታንክ ነው” ያሉት አስተባባሪው ሰራዊቱ “መቀሌን በታንክ ለመክበብ” ከሚያስችል ውጊያ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
ጊዜው “መቀሌ ያለው ህዝባችን ከከባድ መሳሪያ ጥቃት ራሱን እንዲታደግ ጥሪ የሚተላለፍበት ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
እንደ አስተባባሪው ገለጻ ከሆነ “ከዚያ በኋላ ምህረት የለም”፡፡
ህብረተሰቡም በውስጡ የተደበቀውን ኃይል “የግድ ማራቅ ውጣልኝ አታስጨርሰኝ” ማለት ይጠበቅበታል፡፡
“ሰራዊቱ እስካሁን ተዋጊውን የህወሓት ኃይል በመለየት እና የህዝቡን ደህንነት በመጠበቅ በጥንቃቄ ላይ የተመሰረተ ማጥቃት ነበር ሲያካሂድ የነበረው“ ያሉት ኮሎኔል ደጀኔ በመቀሌ ግን እንደዛ ሊሆን እንደማይችል አስታውቀዋል፡፡