መከላከያ ሰራዊቱ በትናንትናው እለት አክሱምን ሙሉበሙሉና አዲግራት ዙሪያን መቆጣጠሩን ገልጾ ነበር
መከላከያ ሰራዊቱ በትናንትናው እለት አክሱምን ሙሉበሙሉና አዲግራት ዙሪያን መቆጣጠሩን ገልጾ ነበር
የመከላከያ ሰራዊት በዛሬው እለት ከመቀሌ በሰሜን ምስራቅ የምትገኘውን የአዲግራት ከተማን ተቆጣጥሮ ወደ መቀሌ እያመራ መሆኑ የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ አዲግራትን ከህወሓት ሃይሎች ነው ነጻ ማውጣቱን ነው የገለጸው፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ በትናንትናው እለት አክሱምን ሙሉ በሙሉ፤ የአድዋና የአዲግራት ዙሪያን መቆጣጠሩን መግልጹ ይታወሳል፡፡ መራጃ ማጣሪያው በትናንትናው እለት መከላከያ ሰራዊት ሽሬን ከያዘ በኋላ ከህወሓት ሃይል የመሸገ ኃይል ገጥሞት ነበር ብሏል፡፡
ትናንት በነበረው ውጊያ ብዛት ያላቸው የህወሓት ተዋጊዎች እዳቸውን መስጠታቸውን መንግስት ገልጿል፡፡
በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ግጭት ያመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥቅምት 24 ህወሓት በትግራይ ክልል ባለው የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሷል፤እርምጃም እንደሚወሰድ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ግጭቱ ከተጀመረ በኋላ በህወሓት በኩል የመደራደር ፍላጎት ቢኖርም መንግስት ወንጀለኛው የህወሓት ቡድን ወደ ህግ ሳይቀርብ ድርድር እንደማኖር በተደጋጋሚ እአገለጸ ይገኛል፡፡ ግጭቱ ከተጀመረ ከሁለት ሳምንት በላይ ሆኖታል፡፡