ግብጽ በበረሃ እየገባቻት ላለችው አዲሷ ዋና ከተማ ምን ያህል ገንዘብ መደበች?
ፕሮደክቱን የሚቆጣጠረው ኩባንያ እንደገለጸው የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ወደ ከተማዋ ገብተዋል
ትርምስ ከበዛባት ካይሮ ርቃ በበረሃ ላይ የተገነባችው አዲሷ ከተማ፣ ለግብጽ የወደፊት የቴክኖሎጂ ሞዴል ትሆናለች ተብሏል
ግብጽ በበረሃ እየገባቻት ላለችው አዲሷ ዋና ከተማ ምን ያህል ገንዘብ መደበች?
ግብጽ ከካይሮ በስተምሥራቅ አቅጣጫ በ48 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ቢሊዮን ዶላሮች በመመደብ አዲስ ዋና ከተማ በመገንባት ላይ ትገኛለች።
ፕሮደክቱን የሚቆጣጠረው ኩባንያ እንደገለጸው የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ወደ ከተማዋ ገብተዋል።
ይህ ፕሮጀክት ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ የኢኮኖሚ እድገት እና እያደገ የመጣውን የህዝብ ፍላጎት ለማሟላት ይጠቅማሉ ካሏቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ነው። ነገርግን ተችዎች የግብጽን የእዳ ጫና ይጨምራል ይላሉ።
ኒው አድሚስትሬቲቭ ካፒታል(ኤንኤሲ) የተባለው ፕሮጀክት ከጀመረ ከስምንት አመት በኋላ የመንግስት ሰራተኞች አዲስ ወደተገነቡት ሚኒስቴር መስሪያቤቶች እና ቢሮዎች ባለፈው ሐምሌ መዛወር ጀምረዋል።
የአድሚስትሬቲቭ ካፒታሉ የከተማ ልማት(ኤሲዩዲ) ሊቀመንበር ካሊድ አባስ "በየቀኑ 48ሺ ሰራተኞች እየመጡ ነው" ብሏል።ዠ
ትርምስ ከበዛባት ካይሮ ርቃ በበረሃ ላይ የተገነባችው አዲሷ ከተማ፣ ለግብጽ የወደፊት የቴክኖሎጂ ሞዴል ትሆናለች ተብሏል።
የግንባታው የመጀመሪያ ምዕራፍ ከአፍሪካ በእርዝመቱ ትልቅ የሆነ ባለ 70 ፎቅ ህንዳ፣ ትልቅ መስጂድ እና የመካከለኛው ምስራቅን ትልቅ ካቴደራል ያካትታል።
ከምስራቅ ካይሮ የሚነሳ የኤልክትሪክ ባቡር ባለፈው አመት መጀመሪያ ላይ ስራ ጀምሯል። እስካሁን 100ሺ ቤቶች የተገነቡ ሲሆን 1200 ቤተሰቦች ተዘዋውረዋል።
ዋናዋና ባንኮች እና ሌሎች ተቋማት በ2024 የመጀመሪያው ሩብ አመት ዋና መቀመጫቸውን ያዛውራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከተማዋን በሶስት ምዕራፍ እንደምትገነባ አባስ ተናግረዋል።
አንደኛው እና ሁለተኛው ምዕራፍ እያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዮን ነዋሪዎች በ168 ሄክታር ላይ እንዲሰፍሩ ያደርጋሉ። ምዕራፍ አንድ ከዚህ አመት ማብቂያ ጀምሮ በ2027 ይጠናቀቃል ተብሏል።
አባስ እንዳሉት ፍላጎቱ እየታየ ምዕራፍ ሶስትም ይጀመራል።
በከተማዋ 10 ኪሎሜትር የሚሸፍን "አረንጓዴ ወንዝ" የተባለ ፖርክን ጨምሮ በርካታ መሰረተልማቶች መልማታቸውን አባስ ተናግረዋል።
ኤሲዩዲ 51 በመቶው በጦሩ እና 49 በመቶው በቤቶች ሚኒስቴር ሲሆን በምዕራፍ አንድ የመሰረተ ልማት እና ህንጻ ግንባታ 500 ቢሊዮን የግብጽ ፖውንድ ወጭ አድርጓል።
ይህ ወጭ 16 በሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጋር ይስተካከላል።
አባስ እንደገለጸው ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ 250-300 ቢሊዮን ፖውንድ ይፈጃል። በ2019 ከአባስ በፊት የነበሩት ኃላፊ አዲሷን ከተማ ለማጠናቀቅ 58 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ ገምተው ነበር።