ምእራብ አፍሪካዊቷ ኢኳቶሪያል ጊኒ የሞት ቅጣት ህግን ሻረች
በአዲሱ የሀገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ የሞት ፍረድ ተሽሯል
ፕሬዝደንት ኦቢያንግ በፈረንጆቹ 2019 የሞት ቅጣትን ለማስቀረት ህግ እያረቀቁ መሆናቸውን ገልጸው ነበር
ምእራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኢኳቶሪያል ጊኒ የመጨረሻውን የሞት ግድያ ከፈጸመች ከሰምንት አመት በኋላ የሞት ግድያ ህግን ሽራለች።
በአዲሱ የሀገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ የሞት ፍረድ መሻሩን ሮይተር ዘግቧል።
አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢኳቶሪያል ጊኒ ዝቅተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት አያያዝ ያለባት ሀገር ነች።
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የውጭ ኃይሎች በፕሬዝደንት ኦቢያንግ የሚመራውን መንግስት በማሰቃየት፣ ምክንያታዊ ባልሆነ እስር እና የውሸት ክስ በማቅረብ ይከሳሉ።
ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል በትንሿ እና ኦይል አምራች በሆነችው ኢኳቶሪያል ጊኒ የመጨረሻው የሞት ቅጣት የተካሄደው በፈረንጆቹ 2014 መሆኑን ገልጿል።
ፕሬዝደንት ኦቢያንግ በፈረንጆቹ 2019 የሞት ቅጣትን ለማስቀረት ህግ እያረቀቁ መሆናቸውን ገልጸው ነበር።
የኘሬዝደንት ኦቢያንግ ልጅ የሆነው ምክትል ኘሬዝደንት ቴዎድሮ ንጉማ ኦቢያንግ መንጉ የሞት ቅጣቱ መሻሩ ታሪካዊ እርምጃ ነው ሲሉ ገልጸውታል።