የኡጋንዳ ጦር አባላቱ በሶማሊያ የአፍሪከ ህብረት ሰላም አስከባሪ ስር የነበሩ ናቸው
በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጥላ ስር የነበሩት አምስት የኡጋዳ ወታደሮች የሞት እና የእስር ቅጣት እንደተፈረደባቸው ተሰምቷል።
ወታደሮቹ ላይ የቅጣት ውሳኔው የተላለፈው ባሳለፍነው ነሃሴ ወር 7 ንጹሃን የሶማሊያ ዜጎችን በመግደል ጥፋጠኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው።
የኡጋንዳ ጦር አባላቱ ባሳለፍነው ቅዳሜ ፍርድ ቤት ቀርበው የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈባቸውም ተነግሯል።
በዚህም ከአምስቱ ወታደሮች ውስጥ ሁለቱ በሞት እንዲቀጡ የተወሰነ ሲሆን፤ ሶስቱ ወታደሮች ደግሞ በ39 ዓመት እስር ኢንዲቀጡ ተፈርዶባቸዋል።
የእስር ቅጣት የተላለፈባቸው ወታደሮቹ የእስር ጊዜያችውን ለመፈፀም ወደ ኡጋንዳ የሚመለሱ መሆኑም ተነግሯል።
የኡጋንዳ ጦር አባላቱ በጎልወይን ግንባር ከአሸባወሪው አልሸባብ ጋር በተደረገ ጦርነት ወቅት ሰላማዊ ዜጎችን በህገ ወጥ መንገድ ገድለዋል ነው የተባለው።
በችሎቱ ላይ የተገኙት የተጎጂ ቤተሰቦች በውሳኔው ደስተኛ መሆናቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ ለተጎጂ ቤተሰቦች ተገቢው ካሳ ይከፈላል ብለው እንደሚጠብቁም ገልፀዋል።
የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ኃይል ላፉት 14 ዓመታ በሶማሊያ ቆይታ አድርጓል።
የሰላም አስከባሪ ኃይሉ በቆይታው በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሰው አሸባሪው አይ ኤስ ጋር እየተዋጋ ሲሆን፤ በአሚሶም ውስጥ ሰራዊት ካዋጡት ሀገራት ውስጥ አንዷ ኡጋንዳ ነች።
የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ኡጋንዳ 20 ሺህ ወታደሮችን ያዋጣች ሲሆን፤ በዚህም በአሚሶም ስር ካለው ጦር ውስጥ አንድ ሶስተኛውን ይሸፍናል።