የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የኔቶ አባልነት ጥያቄን ለመግፋት አንካራን ጎብኝተዋል
የቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን እንደተናገሩት ሩሲያ የጥቁር ባህር የእህል ስምምነትን ቢያንስ ለሦስት ወራት እንድታራዝም ግፊት እያደረጉ ነው።
ፕሬዝዳንቱ በነሀሴ ወር የቭላድሚር ፑቲንን ጉብኝት አስታውቀዋል።
ኤርዶጋን ይህን ያሉት የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት እጣ ፈንታን በሚመለከት ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ተወያይተው በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ባለፈው ዓመት በቱርክ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አደራዳሪነት የተደረሰው ስምምነት የእህል ምርትን ከዩክሬን ወደቦች በጥቁር ባህር በኩል ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችል ነበር።
የዘለንስኪ ጉብኝት የኔቶ ዋና ከተማዎችን የመጎብኘት አካል ሲሆን፤ ፕሬዝዳንቱ በሚቀጥለው ሳምንት በሚደረገው ስብሰባ ላይ የዩክሬን የአባልነት ጥያቄ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ለማበረታታት ነው።
ኤርዶጋን ዩክሬን አባልነቱ ይገባታል ብለዋል።
የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት በሚቀጥለው ወር ፑቲን በቱርክ ከሚነጋገሩበት አጀንዳዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው ብለዋል።
"ተስፋችን በየሦስት ወሩ አንድ ጊዜ እንዲራዘም እንጂ በየሁለት ወሩ እንዲራዘም አይደለም። በዚህ ረገድ ጥረት እናደርጋለን እና የቆይታ ጊዜውን ወደ ሁለት ዓመት ለማሳደግ እንሞክራለን" በማለት አክለዋል።