ፖለቲካ
የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የሶሪያ ወታደራዊ ዘመቻ በአየር ብቻ የተገደበ አይሆንም አሉ
ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በቱርክ የድንበር ከተማ ላይ የተፈፀመውን አደገኛ የሮኬት ጥቃት ተከትሎ በሶሪያ ከአየር ጥቃት ባለፈ ሌላ እርምጃ እያሰላሰሉ ነው ተብሏል
የአንካራ የጦር አውሮፕላኖች እሁድ በሶሪያ እና ኢራቅ በሚገኙ የኩርድ ታጣቂዎች ላይ የአየር ድብደባ ፈጽመዋል
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲጵ ጣይብ ኤርዶጋን በሰሜናዊ ሶሪያ እና ኢራቅ የሚያደርጉት ወታደራዊ ዘመቻ በአየር ጥቃት ብቻ እንደማይገደብ ተናግረዋል።
በቱርክ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ ሰዎች ዋጋ እንደሚከፍሉ ያስገነዘቡት ኤርዶጋን፤ ስለ ተጨማሪ ዘመቻው ያስጠነቀቁት የአንካራ ኃይሎች በሰሜናዊ ሶሪያ እና ኢራቅ በሚገኙ የኩርድ የጦር ሰፈር ላይ የአየር ጥቃትን ከከፈቱ ከአንድ ቀን በኋላ ነው
ፕሬዝዳንቱ በኳታር የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ወደ ተርኪዬ ሲመለሱ "ዘመቻው በአየር ላይ ብቻ የተገደበ እንደማይሆን ምንም ጥርጥር የለውም" ብለዋል።
ኤርዶጋን የምድር ጦር ኃይሎችን ለማሰማራት ውይይት እንደሚደረጉ መናገራቸውን የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
"ብቃት ያላቸው ባለስልጣናት፣ መከላከያ ሚንስቴር እና ሌሎች ኃላፊዎች በአንድነት የምድር ሰራዊታችን ሊጠቀምበት የሚገባውን የኃይል ደረጃ ይወስናሉ" ሲሉ ኤርዶጋን ተናግርዋል።
የቱርክ የጦር አውሮፕላኖች እሁድ በሶሪያ እና ኢራቅ በሚገኙ የኩርድ ታጣቂዎች ላይ የአየር ድብደባ ፈፅመው 89 ኢላማዎችን መውደማቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።