ፕሬዝደንት ጣይብ ኤርዶጋን በሁለት አስርት ዓመታት የስልጣን ዘመናቸው ትልቁን የፖለቲካ ፈተና ይጋፈጣሉ
የቱርክ ፕሬዝዳንታዊ እና የፓርላማ አባላት ምርጫ በበዛሬው እለት እለት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በርካታ ቱርካውያን ለቀጣይ 5 ዓመታት ሀገራቸውን የሚመራ ፕሬዝዳንት እና የፓርላማ ተወካዮቻቸውን ለመምረጥ በማለዳ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በማቅናት ድምጽ እየሰጡ ይገኛሉ።
24 ፓርቲዎችና 151 የግል እጩ ተፎካካሪዎች 600 መቀመጫ ባለው የቱርክ ፓርላማ ወንበር ለማግኘት የመራጮችን ድምጽ ይጠባበቃሉ።