እስራኤል በአለምአቀፉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት መከሰስ አለባት- የቱርኩ ኢርዶጋን
ኢርዶጋን እስራኤል በጋዛ እያደረገች ያለውን ጥቃት "ዘር ማጥፋት" ነው ማለታቸውም ይታወሳል።
የጋዛ የጤና ባለስሌጣናት ባወጡት መረጃ መሰረት እስራኤል በአየር እና በእግረኛ ጦር ባደረሰችው ጥቃት ከ15ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል
እስራኤል በአለምአቀፉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት መከሰስ አለባት ሲሉ የቱርኩ ፕሬዝደንት ኢርዶጋን ተናገሩ።
ኢርዶጋን እስራኤል በጋዛ ፈጽማዋለች ላሉት የጦር ወንጀል በአለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መከሰስ አለባት ሲሉ ለተመድ ኃላፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናገሩ።
የጋዛ የጤና ባለስሌጣናት ባወጡት መረጃ መሰረት እስራኤል በአየር እና በእግረኛ ጦር ባደረሰችው ጥቃት ከ15ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።
እስራኤል ጥቃት የጀመረችው ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር የእስራኤልን ድንበር በመጣስ በ50 አመታት ውስጥ ከባድ የተባለ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነው።
ከተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ጉባኤ አስቀድሞ ባደረጉት የስልክ ንግግር ኢርዶጋን እና ጉተሬዝ "ህጋዊ ባልሆነው የእስራኤል ጥቃት"፣ በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እና በዘላቂ ተኩስ አቁም ዙሪያ ማውራታቸውን የቱርክ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት አስታውቋል።
በንግግሩ ወቅት የቱርኩ ፕሬዝደንት እስራኤል አለምአቀፍ ህግን እና አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ህግን ያለሀፍረት በመጣሷ ለሰራችው ወንጀል በአለምአቀፍ ህግ ፊት ተጠያቂ መደረግ አለባት ብለዋል።
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀካን ፊዳን በኒው ዮርክ በሚካሄደው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ይሳተፋሉ።
ከስብሰባው ጎንለጎን ሚኒስትሩ ከአረብ ሀገራት ከሚመጡ አቻቸው ጋርም ይወያያሉ ተብሏል።
እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን ዘመቻ በጽኑ የምትቃወመው ቱርክ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና በ'ቱ ስቴት ሶሉሽን' ላይ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርባለች።
ኢርዶጋን እስራኤል በጋዛ እያደረገች ያለውን ጥቃት "ዘር ማጥፋት" ነው ማለታቸውም ይታወሳል።
ነገርግን እስራኤል የቱርክን ውንጀላ አትቀበለውም።
በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የነበረው ጦርነት በኳታር አደራዳሪነት ጋብ በማለቱ ታጋቾች እና እስረኞች ተለቀዋል።