በርካታ ተቋማት ለእስራኤል ድጋፍ ያደርጋሉ የሚሏቸውን ድርጎቶች በብዙ ሀገራት እያቆሙ ይገኛሉ
ቱርክ እስራኤልን ይደግፋሉ በሚል ኮካ ኮላ እና ኔስትል ምርቶችን አገደች፡፡
ሐማስ ያልተጠበቀ ጥቃት በእስራኤል ላይ ማድረሱን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት 30ኛ ቀኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን እስራኤል በአየር እና በምድር ላይ ጥቃቷን በጋዛ እያካሄደች ትገኛለች፡፡
በእስራኤል ጦር የተገደሉ ፍልስጤማዊያን ቁጥር ከ10 ሺህ ያለፈ ሲሆን በየዕለቱም 150 ህጻናት እየተገደሉ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
በርካታ ሀገራት እስራኤል ጥቃቷን እንድታቆም የተለያዩ ጫናዎችን በማድረግ ላይ ሲሆኑ ቱርክ በይፋ እስራኤል ጦሯን ከጋዛ እንድታስወጣ በመወጥወት ላይ ትገኛለች፡፡
አሁን ደግሞ የእስራኤል ፓርላማ እስራኤልን ይደግፋሉ በሚል የኮካ ኮላ ምርቶችን ከመጠቀም ማገዱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ የቱርክ ፓርላማ ከኮካ ኮላ በተጨማሪ ቡና እና ማኪያቶ ምርቶች በማቅረብ የሚታወቀው ኔስትል ምርቶችንም እንዳገደ ተገልጿል፡፡
የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን “የእስራኤል ኔታንያሁ አሸባሪ’ ነው፤ ሃማስ አይደለም” አሉ
የቱርክ ፓርላማ የምርቶቹን እገዳ የጣለው በርካታ ቱርካዊያን በማህበራዊ ትስስር ገጾች እርምጃ እንዲወሰድ በዘመቻ መጠየቃቸውን ተከትሎ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ኮካኮላም ሆነ ኔስትል ኩባንያዎች እስካሁን በቱርክ ስለገጠማቸው እገዳ እስካሁን ምላሽ ያልሰጡ ሲሆን በርካታ ሀገራት እና ተቋማት እስራኤል በጋዛ በሚኖሩ ፍልስጤማዊያን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት እየተቃወሙ ይገኛሉ፡፡
የባርሴሎና የወደብ ሰራተኞች ወደ እስራኤል ሊጓጓዝ የነበረን እቃ ወደ መርከብ ላይ አንጭንም ብለው መቃወማቸው ይታወሳል፡፡
እንዲሁም የቤልጂየም ትራንስፖርት ማህበራት ሰራተኞች በተመሳሳይ ወደ እስራኤል ሊላክ የነበረን ድጋፍ ወደ ማጓጓዣዎች እንደማይጭኑ መግለጻቸውን አይዘነጋም፡፡