የሩሲያ እና የዩክሬን መሪዎች ቢገናኙ ቀውሱ ይፈታል- የቱርክ ፕሬዝዳንት
ሩሲያ ፑቲን ዘለንስኪን ከማግኘታቸው በፊት አደራዳሪዎች ስራቸውን መጨረስ አለባቸው ብሎ ነበር
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስድስት ወር አልፎታል
የቱርክ ፕሬዝዳንት ጦርነት ላይ ያሉት የሩሲያ እና ዩክሬን መሪዎች በአካል ቢገናኙ ችግሩ እንደሚፈታ ገለጹ።
ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣኢብ ኤርዶጋሃን፤ የሩሲያንና የዩክሬንን መሪዎች በአካል የማገናኘት ግብ እንዳላቸው አስታውቀዋል። የቱርኩ መሪ ሀገራቱ ወደ ተኩስ አቁም እንዲገቡና ሰብዓዊ እርዳታ ያለገደብ እንዲተላለፍ ማደራደር መጀመራቸው ይታወሳል። በዚህም መሰረት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲተላለፍ ተደርጓል። ይሁንና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራቱ መሪዎች በአካል ቢገናኙ እንደሚመርጡ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪም ቀደም ሲል ጦርነቱን ለማቆም ብቸኛው መፍትሄ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በአካል መገናኘት መሆኑን ገልጸው ነበር። በመቀጠልም ፑቲንና ዘለንስኪ በአካል ሊገያኙ እንደሆነ ሲገለጽ ቢቆይም ክሬምሊን ይህ ለጊዜው አይሆንም ብሏል።
የሩሲያ ቤተ መንግስት (ክሬምሊን) ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፒስኮቭ ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን አቻቸው ጋር በአካል ከመገናኘታቸው በፊት አደራዳሪዎቹ የጀመሩትን ስራ መጨረስ አለባቸው ብለው ነበር።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስድስት ወራት አልፈዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ያላቸውን ጥቃት ከከፈተች በኋላ ምእራባውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ አለ የሚሉትን ማእቀብ ጥለዋል፡
ቱርክ፣ ዩክሬን እና ሩሲያን የማደራደር ሚና እየተወጣች ነው፡፡