ቱርክ ከሩሲያ የምታስገባው ነዳጅ መጠን በእጥፍ መጨመሩ በአውሮፖውያን የተፈጠረውን ክፍተት ሞልቷል
ቱርክ ከአውሮፖ የምታስገባውን ነዳጅ መጠን በእጥፍ በመጨመር በአውሮፖውያን የተፈጠረውን ክፍተት ሞልታለች ተብሏል።
ቱርክ በዚህ አመት ከሩሲያ ያስገባችውን የነዳጅ በእጥፍ መጨመሯ በአውሮፖውያን ገዥዎች የተፈጠረውን ክፍተት መሙላቷን ሮይርስ ዘግቧል።
ሩሲያ የምእራባውያን አጋር በሆነችው ዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" መክፈቷን ተከትሎ አብዛኛውን የሩሲያ ነዳጅ የሚገዙት አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ማእቀብ መጣላቸው ይታወሳል።
ሩሲያ እና ቱርክ በመካከላቸው ያለውን ትብብር ለማስፋት መወሰናቸውን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ንግድ ጨምሯል።
ምእራባውያን በሩሲያ ላይ በጣሉት ማእቀብ ያልታገዱት የቱርክ ኩባንያዎች ከሩሲያ ጋር ንግድ እያደረጉ ነው።
ቱርክ በዚህ አመት እስካሁን 200ሺ በርሜል በላይ ነዳጅ ያስገባች ሲሆን ይህም ሀገሪቱ በፈረንጆቹ 2021 ባለው ተመሳሳይ ወቅት ካስገባችው 98ሺ በርሜል ነዳጅ ጋር ሲነጻጸር ብልጫ አለው።
የቱርኩ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን እና የሩሲያው ኘሬዝደንት ፑቲን ባለፈው ወር በሩሲያዋ የወደብ ከተማ ሶቺ ላይ ንግግር አድርገው ነበር።
መሪዎቹ በስብሰባቸው በሩብል ለመገበያየት መወሰናቸውንም አርቲ በወቅቱ ዘግቦ ነበር።