ስዊድንን ያወገዙ የተቃውሞ ስልፎች
በኢራቅና ሊባኖስ ስዊድን ቅዱስ ቁርአን እንዲቃጠል መፍቀዷን የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሂደዋል
የአረብ ሀገራት ስቶኮልም ተቃዋሚዎች ቅዱስ ቁርአን እንዲያቃጥሉ መፍቀዷን እንድታቆም እያሳሰቡ ነው
በኢራቅና ሊባኖስ ስዊድን ቅዱስ ቁርአን እንዲቃጠል መፍቀዷን የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሂደዋል።
ተቃዋሚዎቹ በሀገራቱ ኤምባሲዎች በመገኘት ስቶኮልም በተደጋጋሚ ጸረ እስልምና አቋም የሚንጸባረቅባቸው ሰልፎች እንዲካሄዱ ይሁንታ መስጠቷን አውግዘዋል።
በቤሩት እና ባግዳድ ቅዱስ ቁርአን ይዘው አደባባይ የወጡት ሙስሊሞች የስዊድን አምባሳደሮች ሀገራቸውን ለቀው እንዲወጡም ነው የጠየቁት።
ኢራንም “ቁርአንን ያራከሱ ሰዎች” ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድባቸው አሳስባለች።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic