ኤርዶጋን 'በጥቁር ባህር የእህል ስምምነት' ጉዳይ ለምምከር ወደ ሩሲያ ሊያቀኑ ነው
ባለፈው አመት በተመድ እና ቱርክ ስምምነቱ እንዲደረስ ያደረጉ ሲሆን ባለፈው ወር ሩሲያ ከስምምነቱ መውጣቷን ማሳወቋን ተከትሎ ስምምነቱ መፍረሱ ይታወሳል
ክሬሚሊን ባለፈው አርብ እለት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በቅርቡ ለመገናኘት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ማስታወቁ ይታወሳል
የቱርኩ ፕሬዝደንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን 'በጥቁር ባህር ስምምነት' ጉዳይ ለመምከር በቅርቡ ወደ ሩሲያ እንደሚያቀኑ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንቱ ወደ ሞስኮ የሚያቀኑት በተመድ አማካኝነት ተደርሶ የነበረው እና ዩክሬን እህል ወደ ወጭ መላክ የሚያስችላት 'የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት' መፍረስን በተመለከተ ውይይት ለማድረግ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባለፈው አመት የመንግስታቱ ድርጅት እና ቱርክ ስምምነቱ እንዲደረስ ያደረጉ ሲሆን ባለፈው ወር ሩሲያ ከስምምነቱ መውጣቷን ማሳወቋን ተከትሎ ስምምነቱ መፍረሱ ይታወሳል።
ቱርክ ሩሲያ ወደ ስምምነቱ የምትመለስበትን እና በዩክሬን ኦዴሳ ወደብ የተከማቸው በ10 ሚሊዮን ቶን የሚቆጠረው ስንዴ ወደ ውጭ እንዲላክ ሩሲያን ለማግባባት አልማለች።
ስምምነቱ ከፈረሰ በኋላ የሩሲያ ሚሳይሎች እና ድሮኖች የዩክሬንን ወደቦች ኢለማ አድርገዋል።
የቱርኩ ገዥ ፖርቲ ኤኬ ቃል አቀባይ ኦመር ክሌክ ኤርዶጋን የሩሲያ የጥቁር ባህር ሪዞርት ሶቺን እንደሚጎበኙ ተናግረዋል። ነገርግን ቃል አቀባዩ ኤርዶጋን ከፑቲን ጋር ስለመገናኘታቸው ያሉት ነገር የለም።
ክሬሚሊን ባለፈው አርብ እለት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በቅርቡ ለመገናኘት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ማስታወቁ ይታወሳል።
ሩሲያ፣ ዩክሬን ያለ ጸጥታ ስጋት እህል ወደ ውጭ መላክ ከሚያስችላት 'የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት' የወጣችው በሩሲያ በኩል የተቀመጡ የስምምነቱ ነጥቦች ተግባራዊ አልሆኑም በሚል ምክንያት ነው።
ሩሲያ እና ዩክሬን እያካሄዱት ያለው ጦርነት በተለይም በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን እንደቀጠለ ነው።