ፖለቲካ
ሩሲያ በጥቁር ባህር በእቃ ጫኝ መርከብ ላይ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ተኮሰች
ሩሲያ ከስምምነቱ የወጣችው በእሷ በኩል ያስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች አልተተገበሩም በሚል ነበር
ሩሲያ ባለፈው ወር በተመድ አማከኝነት የተደረሰውን እና ዩክሬን እህል ወደ ውጭ እንድትልክ ከሚያስችላት "የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት" መውጣቷ ይታወሳል
የሩሲያ ጦር መርከብ በደቡባዊ ጥቁር ባህር ወደ ዩክሬን በማቅናት ላይ በነበረች እቃ ጫኝ መርከብ ላይ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ማሰማቷን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሩሲያ ባለፈው ወር በተመድ አማከኝነት የተደረሰውን እና ዩክሬን እህል ወደ ውጭ እንድትልክ ከሚያስችላት "የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት" መውጣቷ ይታወሳል።
ሩሲያ ከስምምነቱ የወጣችው በእሷ በኩል ያስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች አልተተገበሩም በሚል ነበር።
ሩሲያ ወደ ዩክሬን የሚያመሩ ሁሉንም መርከቦች የጦር መሳሪያ ጭነዋል የሚል ግምት እንደምትወስድ ገልጻለች።
ሩሲያ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ያሰማችው የመርከቧ ካፒቴን እንዲቆም ተጠይቆ ባለመቆሙ ነው ብላለች።
ሮይተርስ የመርከቧን ባለቤት ለማነጋገር ሞክሮ እንዳልተሳካለት ገልጿል።
ሱኩራ ኦካን የተሰኘችው መርከብ ወደ ዩክሬኗ እዝሜል ወደብ እያመራች ነበር ብሏል ሚኒስቴሩ።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በተከታታይ ተኩስ የተተኮሰው መርከቧን በኃይል ለማስቆም መሆኑን ገልጿል።
ጦርነት የገጠሙት ሩሲያ እና ዩክሬን የአለም ከፍተኛ የስንዴ አምራቾች እና ላኪዎች ናቸው።