ኤርትራ ወደ ኢጋድ ልትመለስ መሆኑን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስታወቁ
የኬንያው ፕሬዝዳንት፤ ኤርትራ ለሶማሊያ ሰላም እያበረከተችው ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል
ኤርትራ በኢጋድ አባል ሀገራት በደረሰባት ተቃውሞ ከአባልነት ወጥታ መቆየቷ ይታወሳል
ኤርትራ ላለፉት በርካታ አመታት ርቃው ወደ ነበረው የቀጠናውን ተቋም የምራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ልትመለስ መሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስታወቁ፡፡
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኬንያ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኬንያው አቻቻው ዊሊያም ሩቶ ጋር በመሆን በሰጡት መግለጫ ፤ ዊልያም ሩቶ ወደ ኢጋድ እንደሚለሱ ላቀረቡላቸው ጥያቄ “ቢዘህ ጉዳይ ጥያቄ የለም” ሲሉ ጥያቄውን መቀበላቸውን ተናግረዋል፡፡
- ሶማሊያ በኤርትራ ሲሰለጥኑ የቆዩትን ወታደሮቿን ማስመለስ ጀመረች
- በኤርትራ የሚገኙት የሶማሊያ ወታደሮች በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ሀገራቸው መመለስ ይጀምራሉ- የሶማሊያ ፕሬዝዳንት
"ቀጣናዊ ውህደትን የሚለውን ሃሳብ ይበልጥ ለማጠናከር ወደ ኢጋድ እንደመለሳለን" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ፤ በሀገራቱ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ትብብርም ቢሆን ከቀጠናዊ ውህድት ውጭ ሊሳካ እንዳማይችል አንስተዋል፡፡
"አዲስ ነገር እንፈጥራለን ማለት ሳይሆን ፤ በአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ስም እውነተኛና ውጤታማ ቀጠናዊ ተቋም እንዲኖር ማድረግ ግዴታችን ነው" ሲሉም ነው የተገሩት፡፡
ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ " የማረጋግጥላቸው ነገር ቢኖር. . .ከአሁን በኋላ እንደከዚህ ቀደሙ አይነት ነገር አይኖርም "ም ብለዋል፡፡
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በበኩላቸው የኤርትራ ወደ ኢጋድ መመለስ ቀጠናው ላይ ተጽእኖ ሚፈጥሩ ጉዳዮችን በማስወገድ ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
ኤርትራ በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የምትዳርገውን ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በአብነት በማንሳት፡፡
በኤርትራ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ 5000 ሶማሊያውን ወታደሮች ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በቅርቡ ነበር፡፡
ወታደሮቹ ከኤርትራ መልስ በጸረ-አልሸባብ ዘመቻ ላይ ተሳትፈው አሸባሪው ቡድን ቁልፍ ይዞታዎችን እንዲለቅ በማድረግና በማዳከም ረገድ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኙም እንዲሁ ይታወቃል፡፡
የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከወራት በፊት ከአል-ዐይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኤርትራ ዳግም ወደ ኢጋድ አባልነት ለመመለስ ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጸው እንደነበር አይዘነጋም።
ዋና ጸሃፊው:“ኤርትራ ወደ ኢጋድ ልትመለስ የምትችልበት ሁኔታ ይኖራል፤ንግግር እያደረግን ነው ያለነው”ም ነበር ያሉት በወቅቱ፡፡
እንደፈረንጆቹ በ1993 ነጻነቷን ያወጀችው ኤርትራ በዋናነት የአንበጣ ወረርሺኝን ለመመመከት በሚል ወቅቱ የተቋቋመውን ኢጋድ እንደሚሰረት ከፍተኛ ሚና የተጫወተች ሀገር ነበረች፡፡
በፈረንጆቹ 2007 ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) እራሷን ያገለለችው ኤርትራ እንደገና በ2011 ቡድኑን ተቀላቅላ በኢጋድ አባል ሀገራት በደረሰባት ተቃውሞ ለ2ኛ ጊዜ ከአባልነት መውጣቷም የሚታወስ ነው፡፡