ኤርትራና ቻይና የአሰብና ምፅዋ ወደቦችን በጋራ ለማልማት ከስምምነት ደርሰዋል
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኤርትራ ይፋወዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
በትናትናው እለት የኤርትራ አስመራ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በቆይታቸውም የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ የተላከ መልእክት ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈረወርቂ ማቀበላቸውን የኤርትው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።
በመልእክቱም የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ፐሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቻይና ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ ማቅረባቸውንም አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በውይይቱ ወቅት ቻይና ለኤርትራ ተጨማሪ የ100 ሚሊየን ዩዋን ድጋፍ ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በበኩላቸው የቻይናን የ100 ዓመታት የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ጉዞ እና በዓለም ዐቀፍ ሕጎች ማዕቀፍ ውስጥ ሆና ዓለምን ሚዛናዊ ለማድረግ የምታደርውን ጥረት አድንቀዋል።
ሁለቱ ወገኖች በማዕድን ልማት፣ በምፅዋና አሰብ ወደቦች ልማት፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራትም ከስምምነት ደርሰዋል።
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከኤርትራው አቻቸው ኦስማን ሳሌህ ጋር ከተወያዩ በኋላ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውንም የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።