የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ ያዘጋጁታል
ፊፋ ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር 11 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት አቅጃለሁ ብሏል።
በሜክሲኮ፣ ካናዳ እና አሜሪካ ሀገራት የሚዘጋጀው ይህ ውድድር 48 ቡድኖች የሚሳተፉበት ውድድር ከፍተኛ የገቢ ጭማሪ እንደሚገኝ ከወዲሁ ተነግሯል።
አርብ ለፊፋ ምክር ቤት የቀረበው የአራት ዓመት በጀት 50 በመቶ የሚጠጋ የገቢ ጭማሪ በዋናነት ከቴሌቪዥን እና ከስፖንሰርሺፕ ስምምነቶች ጋር የተቆራኘ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም በውድድሩ ላይ ትኬቶች ሽያጭና የመስተንግዶ ገቢ አይን ተጥሎበታል።
የፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ከምክር ቤቱ ስብሰባ በኋላ “እኛ ስለ እግር ኳስ ኃይል ጠንካሮች ነን" ብለዋል።
"የጨዋታው ተጽእኖ ትልቅ እንደሚሆን እርግጠኞች ነን" ማለታቸውን የዘገበው አሶሼትድ ፕረስ፤ ፊፋ በተለምዶ "ወግ አጥባቂ" የበጀት ግምትን ያደርጋል ነገር ግን ኢላማውን በልክ አይተኩስም ብሏል።
ፊፋ ከፈረንጆቹ 2019 እስከ 2022 የንግድ ዑደት ያሳወቀዉ የ7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ከትንበያው 1 ቢሊዮን ዶላር ብልጫ አለው ተብሏል።
በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ምን ያህል ጨዋታዎች እንደሚደረጉ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን፤ ከ48 ሀገራት ጨዋታዎች ምን ያህሉ "ለብሮድካስተሮች እንደሚሸጡ" እርግጠኛ አይደለንም ተብሏል።
እሁድ የሚጠናቀቀው የ2022 ዋንጫ አርጀንቲና እና ፈረንሳይ ለፍፃሜ በሚፋጠጡበት ውድድር 64 ጨዋታዎች ተደርገዋል።