የተመድ ሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ኤርትራን ጨምሮ 18 ሀገራትን አባል አድርጎ መምረጡን አስታውቋል
ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት አባል በመሆን ከፈረንጆቹ 2022 እስከ 2024 ለማገልገል በድጋሚ በመመረጧ የኤርትራ መንግስት ከፍተኛ ክብርና ደስታ እንደተሰማው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት የተመድ አንድ አካል ሆኖ የተቋቋመ ሲሆን በልማትና በአለምአቀፍ ህጎችና መርሆች እንዲከበሩ ይሰራል፡፡
የኤርትራን የምክርቤቱ አባል ሆና እንድትመረጥ የአፍሪካ ህብረት መደገፉን የገለጸው መግለጫው በአዲሱ ምርጫ መሰረት ኤርትራ በጄኔቫ መቀመጫውን ባደረገው ም/ቤት ለሶስት አመታት ያህል ታገለግላለች ብሏል፡፡
ኤርትራ ከረጅምና አድካሚ ትግል በኋላ ነጸ መውጣቷን ለነጻነት፣ለፍትህና ለእኩልነት ትልቅ ቦታ የሚሰጥ ማህበረሰብ አላብት ብሏል መግለጫው፡፡ መግለጫው ኤርትራ ለዜጎች መብት ታትራ እየሰራች መሆኑንና በዚህም በትምህርት፣ በጤና፣በግብርና ምርታማነት፣ በድህነት ቅነሳና በመሰረተ ልማት ግንባታ መሻሻሎች መታየታቸውን ጠቅሷል፡፡
እንደማንኛው የተመድ አባል ሀገር ኤርትራ በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ዙሪያ ችግሮች እንዳሉባት የገለጸው የኤርትራ መንግስት ለዜጎቹ የሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል መስራት እንዳለበት ገልጿል፡፡ የኤርትራ መንግስት የሰብአዊ መብቶችን ለመጠበቅ አለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችን ፈርማለች፡ለየሰብአዊ መብቶችን ለመጠበቅ አለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችን ፈርማለች፡፡
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በትናንትናው እለት አሜሪካን፣ አርጀንቲናን፣ቤኒንን፣ካሜሮንን፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስን፣ ጋምቢያንና ህንድን ጨምሮ 18 ሀገራትን የተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት አባል አድርጎ መርጧል፡፡