ፖለቲካ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት ዙሪያ ለኤርትራ ገለፃ አደረጉ
ከዚህ ቀደም ኤርትራ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያን በመደግፍ ድምጽ መስጠቷ ይታወሳል
በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልዑክ በሩሲያ ጉብኝት እያደረገ ነው
በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ የተመራ ልኡክ በሩሲያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።
በጉብኝቱ ላይም ከውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ በተጨማሪ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ የማነ ገብረአብ ተገኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅትም የኤርትራ ልኡክ ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ተነግሯል።
በዚህም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፤ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት ዙሪያ ገለጻ ያደረጉላቸው ሲሆን፤ በዚህም የጦርነቱ መነሻ፣ የሩሲያ አቋም እና አሁን ያለበት ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከዚህ ቀደም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያን ከሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ለማገድ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ኤርትራ ሩሲያን በመደግፍ ድምጽ መስጠቷ ይታወሳል።
በተጨማሪም ኤርትራ በተለያ መንገዶች ለሩሲያ ያላትን አጋርነት ስንተልጽ መቆየቷ ይታወሳል።