የኤርትራ መንግስት አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ "የተሳሳተ ፖሊሲ" ስታራምድ ቆይታለች አለ
አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ የምትከተለውን ፓሊሲ እንድታሻሽል ኤርትራ ጥሪ አቀረበች
ኤርትራ የዋሽንግተን-አስመራ ግንኙነት "ከታሰበለት ሀዲድ እንደማይወጣ ተስፋ አደርጋለሁ" ብላለች
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት በድረገጹ ባወጣው መግለጫ፤ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ባራክ ኦባማ፣ ጆርጅ ቡሽን እንዲሁም ቢል ክሊንተን በአፍሪካ ቀንድ ይከተሉት ነበር ያለውን "የተሳሳተ ፖሊሲ" ነቅፏል፡፡
ሚኒሰቴሩ በአፍሪካ ቀንድ የሚስተዋለው የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት “ የህዘቦችን ሉአላዊነት የሚደፈጥጥ፣ዓለም አቀፍ ህጎችን የሚጥስ፣ በኃይልና ማስፈራራት የተሞረኮዘ፣ በቀጠናዊ ተቋማት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር እንዲሁም በአከባቢው ግጭቶችን የሚያስነሳ” ነው ሲል ይወቅሳል፡፡
"እነዚህ የተሳሳቱ ፖሊሲዎች በአፍሪካ ቀንድ ባጠቃላይ በእያንዳነድ ሀገራት ደግሞ በተለይ ከባድ ቀውስ አስከትለዋል" በማለትም አክለዋል ሚኒሰቴሩ በመግለጫ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኃላፊነት መምጣታቸውን ተከትሎ፤ የኤርትራ መንግስት የተሳሳቱ ናቸው ያለቸውን ፖሊሰዎች ለማስተካከል ብዙ ርቀት መሄዱንና በመፍትሄዎች ላይ የሚያጠነጥን "ሰነድ" ማስረከቡንም የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አስታውቀዋል፡፡
ምንም እንኳ ሚኒስቴሩ ለአሜሪካ አስረከብኩት ስላለው ሰነድ ዝርዝር ይዘት ያለው ምንም ነገር ባይኖርም፡፡
አሁን የተጀመረው ጥረት"ከታሰበለት ሀዲድ እንደማይወጣ ተስፋ አደርጋለሁኝ" እናም ሊሻሻል ይገባልም ብለዋል ሚኒሰቴሩ ትላንት ባወጣው መግለጫ፡፡
ወደ ዝቅተኛ ደረጃ ወርዶ የነበረው የኤርትራና አማሪካ ግንኙነት በዶናልድ ትራምፕ የስልጣን ዘመን የተወሰነ መሻሻያዎች ማሳየት ችሎ ነበር፡፡
የአሜሪካ አንጋፋ ዲፕሎማቶች አምባሳደር ዶናልድ ያማማቶ ቀጥሎም እሳቸውን የተኩት አምባሳደር ቲቦር ናዥን ከረዥም ጊዜ በኋላ በኤርትራ ያደረጉት ጉብኝት የሚጠቀስ ነው፡፡