አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ
አቶ ኢሳያስ ጅራ በድጋሚ ሊመረጡ የቻሉት የጠቅላላ ጉባኤውን 94 ድምጽ በማግኘት ነው
አቶ ኢሳያስ ጅራ "የሊግ ውድድሮች የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲያገኙ አደርጋለሁ" ሲሉ ቃል በመግባታቸው ይታወሳል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ14ኛው ጠቅላላ ጉበዔው አቶ ኢሳያስ ጅራን በድጋሚ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል፡፡
አቶ ኢሳያስ ጅራ በድጋሚ ሊመረጡ የቻሉት የጠቅላላ ጉባዔውን 94 ድምጽ በማግኘት ነው፡፡
ሌሎች ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው የቀረቡት የአማራ ክልል ተወካዩ አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምጽ እንዲሁም የድሬድዋ ተወካዩ አቶ ቶኪቻ አለማየሁ 17 ድምጽ ማግኘታቸውም ተገልጿል።
ጠቅላላ ጉባዔው ከፕሬዝዳንት ምርጫው በተጨማሪ ከ35 ዕጩዎች 11 የሥራ አስፈፃሚ አባላትን እንዲሁም ምክትል የፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት መርጧል።
አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነ ሊሰሩ የሚችሏቸውን ተግባራት በተመለከተ ባሳለፍነው ረቡዕ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ/ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በድጋሚ የምምረጥ ከሆነ "ብሔራዊ ሊግን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የሊግ ውድድሮች የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲያገኙ" እንደሚያደርጉ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
አቶ ኢሳያስ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ቢመረጡ የፌዴሬሽኑን ተቋማዊ አደረጃጀት ከማጠናከር በዘለለ፣ ከሊግ ካምፓኒው ጋር በመተባበር "ክለብ ላይሰንሲንግ" ላይ ለመስራት፣ ተጨማሪ የልምምድ ስፍራዎችን ለመገንባት፣ የአሰልጣኞችን አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ስልጠናዎችን ለመስጠት ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ላይ ከመስራት እና ለክልል ፌዴሬሽኖች የተሻለ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር የሙያ ማህበራትን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ብሔራዊ ሊግ እና ሱፐር ሊግን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ ውድድሮች የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲኖራቸው ለማድረግ እሰራለሁም ነው አቶ ኢሳያስ ያሉት፡፡
ለዚህ የሚሆንና ለቀጣዮቹ 4 ዓመታት የሚያገለግል "ሌጋሲ ዶክመንት" አዘጋጅተናል ብለዋል፡፡
የተጫዋቾች ዝውውር መነሻውን ከ2 ዓመት ከፍ በማድረግና ጣራውን እስከ 5 ዓመት በማድረግ የተረጋጋ የኮንትራት ይዞታን ለመፍጠር እንደሚሰሩም ነው መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡
አቶ ኢሳያስ ጅራ በድጋሚ ሊመረጡ የቻሉት የጠቅላላ ጉባዔውን 94 ድምጽ በማግኘት ነው፡፡
ሌሎች ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው የቀረቡት የአማራ ክልል ተወካዩ አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምጽ እንዲሁም የድሬድዋ ተወካዩ አቶ ቶኪቻ አለማየሁ 17 ድምጽ ማግኘታቸውም ተገልጿል።
ጠቅላላ ጉባዔው ከፕሬዝዳንት ምርጫው በተጨማሪ ከ35 ዕጩዎች 11 የሥራ አስፈፃሚ አባላትን እንዲሁም ምክትል የፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት መርጧል።
አቶ ኢሳያስ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነ "ብሔራዊ ሊግን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የሊግ ውድድሮች የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲያገኙ" እንደሚያደርጉ ነሀሴ 18፣2014ዓ.ም መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡